የዘርፉ ባለሙያዎች “አጓጊ ግን የከሸፈ የመርከብ ጽንሰ-ሀሳብ” ይሉታል
አሜሪካ ካላት ግዙፍ የጦር መሳሪያዎች ውስጥ “ዩ.ኤስ.ኤስ ዙምዋልት” የጦር መርከብ አንዱ እንደሆነ ይነገራል።
4 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደወጣበት የሚነገረው የጦር መርከቡ በርካታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎቸን የጣጠቀ እንደሆነ ይነገርለታል።
በፈረንጆቹ 2008 ግንባታው የተጀመረው የጦር መርከቡ በ2013 ላይ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2016 ላይ በአሜሪካ ባህር ኃይል ስራ ላይ እንደዋለም መረጃዎች ያመለክታሉ።
አሁን ላይ አሜሪካ ሁለት ዙምዋልት አውዳሚ የጦር መርከቦችን ያላት ሲሆን፤ እነዚህ “ዩ.ኤስ.ኤስ ሞንሶር” እና “ዩ.ኤስ.ኤስ ላይደን ቢ ጆንሰን” የሚል መጠሪያ ያላቸው ናቸው።
አውዳሚ ነው የተባለው የጦር መርከቡ አሜሪካ ካላት ጦር መርከቦች የወጣበት ዋጋ በእጥፍ የሚበልጥ ነው ብለዋል።
የቢላዋ ቅርጽ ያለው የመርከቡ የፊት ክፍል በከባድ የባህር ክፍል ላይ በቀላሉ እንዲጓዝ የሚያስችለው መሆኑንም ድፌንስ ኒውስ በመረጃው አስታውቋል።
መርከቡ 158 የባህር ኃይል አባላትን አሳፍሮ የሚጓዝ ሲሆን፤ 16 ሺ ቶን ገደማ ክብደት በመያዝ በሰዓት እስከ 56 ኪሎ ሜትር መብረር ይችላል ተብሏል።
መርከቡ ባለብዙ ተግባር ራዳሮች የተገጠሙለት ሲሆን፤ ከውኃ አካል ላይ ወደ ላይ ሚሳዔል ለማስወንጨፍ የሚያስችሉ 80 ሴሎች እንዳሉትም ተነግሯል።
ሆኖም ግን መርከቡ የፀረ መርከብ፣ የፀረ ባሀር ስርጓጅ ፣ የአየር መከላከያ ሚሳዔሎችን ማስወንጨፊያ የሌለው መሆኑ እንደክፍተት ይነሳበታል።
የወታደራዊ ጉዳዮች ባለሙያ የሆኑት ሴባስቲያን ሮብሊን፣ የመርከቡ ጽንሰ ሀሳብ እጅግ አጓጊ ነገር ግን የከሸፈ ነው ሲሉ ይገልጹታል።