በቂ እንቅልፍ አለመተኛት ከየትኛውም ህመም በላይ ገዳይ መሆኑን ያውቃሉ?
ዓለም አቀፉ የእንቅልፍ ቀን ትናንት ተከብሯል
በቂ እንቅልፍ አለመተኛት ከልብ ህመም ጋር ለተያያዙ በርካታ በሽታዎች ያጋልጣል
በቂ እንቅልፍ አለመተኛት ከየትኛውም ህመም በላይ ገዳይ መሆኑን ያውቃሉ?
ሁሌም በየዓመቱ በጎርጎሮሲያዊያን ዘመን አቆጣጠር ጥር ሶስት የዓለም እንቅልፍ ቀን ተብሎ የሚከበር ሲሆን ዕለቱ ስለ እንቅልፍ ጠቀሜታነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ስራዎችን በመስራት ታስቦ ይውላል።
እንደንተመራማሪዎች ገለጻ እንቅልፍ ለአዕምሮ ንቃት እና ብርታት አስፈላጊ ሲሆን ይህን አለማድረግ ደግሞ ለብዙ የጤና እክሎች ይዳርጋል።
በቂ እንቅልፍ አለመተኛት የመጀመሪያው ጉዳት ከልብ ጋር ለተያያዙ ችግሮች ይዳርጋልብየተባለ ሲሆን ለአብነትም ለልብ ህመም፣ ለልብ ምት መቆም እና ለደም ግፊት እንደሚያጋልጥ ተገልጿል።
ሁለተኛው በቂ እንቅልፍ ያለመተኛት ጉዳት ለትኩረት ማጣት እና አዕምሮ መዛል ነው ተብሏል።
በቂ እንቅልፍ የሚባለው ሀሳብ አጨቃጫቂ ሲሆን ተመራማሪዎች ግን በቂ እንቅልፍ ጊዜን በእድሜ ከፋፍለው ያስቀምጡታል።
እድሜያቸው ከ14-17 የሆኑ ታዳጊዎች በቀን ከ8 እስከ 10 ሰዓታት መተኛት አለባቸው የተባለ ሲሆን አዋቂዎች ደግሞ ከ7 እስከ 9 ሰዓት ድረስ እንዲተኙ ይመከራሉ።
ህጻናት ደግሞ በቀን ከ12-16 ሰዓታት እንዲተኙ የሚመከር ሲሆን ሰዎች ለእንቅልፋቸው ትኩረት እንዲሰጡ ተመራማሪዎች ይመክራሉ።
የመኝታ ክፍሎችን ለእንቅልፍ ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ንጹህ አየር ማናፈስ፣ ወደ መኝታ ክፍል ከመግባት በፊት ከኤሌክትሮኒክስ እና አነቃቂ መጠጦች ከመጠቀም መታቀብ ረጅም ጊዜን በእንቅልፍ ውስጥ ለመቆየት ይረዳልም ተብሏል።
እንዲሁም ንጽህናን መጠበቅ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ አለመግባባቶችን ወደ መኝታ ክፍል ይዞ አለመግባት፣ ምቹ የሌሊት ልብሶችን መልበስ እና ጸሎት ማድረግ በቶሎ እንቅልፍ እንዲወስደን ከሚረዱ መንገዶች መካከል ይጠቀሳሉ።