ዓለም ከዉሀን መነሳሳትን መውሰድ አለበት-ዶ/ር ቴድሮስ
የኮሮና ቫይረስ እ.ኤ.ኤ በ2019 ታህሳስ ወር ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ በዉሀን መከሰቱ ሪፖርት የተደረገው
ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ ቫይረሱን ለማስቆም ከቻይናዋ ዉሀን ከተማ መነሳሳትን መውሰድ ይገባል ብለዋል
ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ ቫይረሱን ለማስቆም ከቻይናዋ ዉሀን ከተማ መነሳሳትን መውሰድ ይገባል ብለዋል
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለማስቆም ሀገራት ከቻይናዋ ውሀን ከተማ መነሳሳትን መውሰድ እንዳለባቸው ማስገንዘባቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ ትናንት በሰጡት መግለጫ በቻይናዋ ከተማ የተገኘው ውጤት ሀገራት ቫይረሱን እንደሚያሸንፉት የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው ብለዋል፡፡
“ከባድ ሁኔታዎች ሊቀየሩ እንደሚችሉ ውሀን ለተቀረው አለም ተስፋ ሰጥታለች፤ ጥንቃቄዎችን መለማመድ አለብን፡፡ ሁኔታው ከባድ ሊሆን ይችላል ነገርግን ከተሞችና የሀገራት ልምድ የሚያሳየን ቫይረሱን መጋፈጥ ለተቀረው አለም ተስፋንና መነሳሳትን ይሰጣል፡፡ በእያንዳንዱ ቀን ሰለቫይረሱ እየተማርን ነው” ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስ ተደምጠዋል፡፡
ኃላፊው መግለጫውን የሰጡት ከቻይናዋ ዉሀን ከተማ ግዛት ምንም አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው የሚያሳይ ሪፖርት አለመቅረቡን ተከትሎ ነው፡፡
የኮሮና ቫይረስ እ.ኤ.ኤ በ2019 ታህሳስ ወር ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ በዉሀን መከሰቱ ሪፖርት የተደረገው፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት ወረርሽኝ የተባለው ቫይረሱ እስካሁን ከ10000 በላይ ለሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት ሲሆን ከ250000 በላይ የሆኑ ሰዎችን ደግሞ አጥቅቷል፡፡