የተሰረቀን ሞባይል ለማስመለስ ከእንግሊዝ ቻይና የተደረገ አደን
በእንግሊዝ እና ዌልስ በክፈተኛ ደረጃ እየጨመረ የሚገኝው የሞባይል ስርቆት ነዋሪዎችን አማሯል
በዋና ከተማዋ ለንደን ባለፉት 5 አመታት የሚፈጸሙ የስልክ ስርቆቶች በ73 በመቶ ጨምረዋል
አካራ ኢታህ የተባለው እንግሊዛው ባሳለፍነው ሚያዚያ በማዕከላዊ ለንደን በሚገኝ የመሬት ውስጥ ባብሩ ጣብያ ነበር በሞተረኞች አይፎን 13 የሞባይል ስልኩን የተመነተፈው፡፡
ግለሰቡ ስልኩን ለማስመለስ መንታፊዎችን በሩጫ ለጥቂት ርቀቶች መከታተል ቢችልም በፍጥነት ከአይኑ ይሰወሩበታል፡፡
ቤቱ ውስጥ ከገባ በኋላ አይፎን ስልኮች ላይ በሚገኝው “ፋይንድ ማይፎን” ስልኩ እንደተጠፋ መረጃውን በመሰጠት ሞባይሉ የሚገኝበትን ቦታ መከታተል ይጀምራል፡፡
ለስምንት ቀናት በተለያዩ የለንደን ክፍሎች ስልኩ የሚገኝበትን ጂፒኤስ በመከተል ሙከራ ሲያደርግ ቆይቶ በመጨረሻም ከሀገር ውጪ መውጣቱን ይረዳል፡፡
ከአንድ ወር በኋላ ስልኩ የሚገኝበት ስፍራ መልዕክት ሲመለከት የሞባይል ቀፎው ቻይና ሽንዥን ግዛት መግባቱን ሲያውቅ ተስፋ ቆርቶ ትቶታል፡፡
ኢካራ ለስምንት ቀናት በተለያዩ የለንደን ክፍሎች ስልኩን እየተከታተለ በሚገኝበት ጊዜ ለፖሊስ ተደጋጋሚ ጥቆማ ቢሰጥም ፖሊስ ሊያግዘው ፈቃደኛ እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡
ይልቁንም ሞባይሉን ማስመለስ የሚፈልግ ከሆነ ጥቅም ላይ የዋሉ ቁሳቁሶች ለገበያ የሚቀርቡባቸው ገበያዎችን ቢያማትር ስልኩን ሊያገኝው እንደሚችል ከፖሊስ ምክር እንደተሰጠው ተነግሯል፡፡
ኢካራ የሞባይል ስልኩን ለመግዛት ለረጂም ጊዜ ገንዘብ እንዳጠራቀም እንዲሁም በውስጡ በርካታ የቢዝነስ እና የወዳጆች መረጃዎች ይገኙበት እንደነበር ገልጿል፡፡
ብሪታንያ የተወሰኑ የጦር መሳርያ አይነቶች ለእስራኤል እንዳይሸጡ ከለከለች
ሌቦቹ ስልኩን ከፍተው መጠቀም ስለማይችሉ ለመለዋወጫነት ብቻ እንደሚጠቀሙበት ሳስብ እበሳጫለሁ ነው ያለው፡፡
የሞባይል ስርቆት ማዕከል ሆናለች በምትባለው ለንደን በየስድስት ደቂቃው ልዩነት አንድ ስልክ የሚሰረቅ ሲሆን በ2019 165 ሺህ933 ስልኮች መሰረቃቸውን ለፖሊስ ሪፖርት እንደቀረበ ነው የተነገረው፡፡
ባለፉት አምስት አመታት በዋና ከተማዋ የሚደረጉ የስልክ ስርቆቶች በ73 በመቶ መጨመሩን የገለጸው የለንደን ፖሊስ በተለይ ቱሪስቶች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ስርቆቱ እንደጨመረ አስታውቋል፡፡
ዌስትሚንስትር እና ኒውሀም በተባሉ ስፍራዎች በተደጋጋሚ የሚፈጸሙ ስርቆቶችን ለመከላከል ፖሊስ እራሱን የቻለ ግብረ ሀይል ማቋቋሙንም ይፋ አድርጓል፡፡
ነገር ግን ስርቆቱን የሚፈጽሙት ግለሰቦች በሚጠቀሙት ሞተር ሳይክሎች የሚገቡባቸው ስፍራዎች እና በፍጥነት የስልኮቹን አካላት በታትነው ለመለዋወጫነት ጥቅም ላይ ማዋላቸው ወንጀለኞችን ለመያዝ አስቸጋሪ እንዳደረገው ገልጿል፡፡