በሺህ የሚቆጠሩ ኢራናውያን የበርካታ ንጹሃን ደም የፈሰሰባትን አርብ እለት በተቃውሞ አከበሩ
የኢራናዊት ኩርድ ማህሳ ሞት በኢራን ታይቶ የማይታወቅ የተቃውሞ ማዕበል መቀስቀሱ ይታወቃል
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የጸጥታ ሃይሎች በተቃዋሚዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ 66 ሰዎችን ተገድለዋል ብሏል
በሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን መስከረም 30 በጸጥታ ሃይሎች በተወሰደው እርምጃ በርካታ ንጹሃን ህይታቸውን ያጡበትንና “የደም አርብ” የተባለውን ቀን በትናንትናው አርብ እለት በተቃውሞ አክብረውት ብለዋል፡፡
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ የጸጥታ ሃይሎች በወርሃ መስከረም በሲስታን እና በባሉቺስታን ግዛት ዋና ከተማ ዛሄዳን በተቃዋሚዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ 66 ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ተገድለዋል።
በማህበራዊ የትስስር ገጾች በርካታ ተከታዮች ያሉት 1500ታስቪር በመባል የሚታወቀው አክቲቪስት በትዊተር ገጹ ላይ ለጠፈው ቪዲዮም አርብ እለት በሺዎች የሚቆጠሩ በዛሄዳን በድጋሚ ሰልፍ ሲወጡ የሚያሳይ ነው፡፡
1500ታስቪር በደቡብ ምስራቅ ከምትገኘው ካሽ ከተማ ነው ያለው ሌላው ቪዲዮ ተቃዋሚዎች እንደፈረንጆቹ በ2020 በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ኢራቅ በተፈጸመ ጥቃት የተገደለውን የከፍተኛ ጄኔራል ቃሴም ሱሌይማኒ ስም ያለበት ጽሁፍ ይዘው የመንገድ ላይ ምልክቶች ሲረግጡ እና ሲሰብሩ ያሳያል።
የ22 ዓመቷ ኢራናዊት ኩርድ ማህሳ ጸጉርሽን በትክክል አልሸፈንሽም በሚል በቴህራን የደንብ አስከባሪ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ከዋለች ከሶስት ቀናት በኋላ በእስር ላይ እያለች ህይወቷ ማለፉ የሚታወስ ነው።
የማህሳ አሚኒ ሞት ታዲያ በኢራን ታይቶ የማይታወቅ የተቃውሞ ማዕበል ቀስቅሷል።
ተቀውሞው እንደፈረንጆቹ በ1979 በአሜሪካ የሚደገፈውን ሻህ ከስልጣን ለማስወገድ ከተደረገው የእስልምና አብዮት ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች (አብዛኛዎቹ እና አክቲቪስቶች) የሞቱበትም ሆነዋል፡፡
ይህም በኢራን ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ ተደረገው የሚታዩት አያቶላ አሊ ካሜኒ እንደዚህ አይነት ተቃውሞ ሲገጥማቸው የመጀመሪያው መሆኑም ጭምር ይገለጻል፡፡
በሁኔታው የተደናገጡት የቴህራን ባለስልጣናት በሀገሪቱ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ የአሜሪካ እጅ እንዳለበት ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡
የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከሳምንታት በፊት ባደረጉት ንግግር አሜሪካ በሀገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ሽፋን በማድረግ ቴህራንን “የማተራመስ ፖሊሲ” እየተገበረች ነው መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
ይሁን እንጅ የአሜሪካ ሴራ ሊሳካ እንዳመይችልና እንደከሸፈ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ መናገራቸው ኤኤፍፒ የኢራን ሚዲያ ጠቅሶ በቅርቡ መዘገቡ አይዘነጋም፡፡
ኢብራሂም ራይሲ “እንደፈረንጆቹ በ2011 በኢስላሚክ ሪፐብሊክ የተካሄደውን የአረቦች ህዝባዊ አመጽ ለመድገም አሜሪካ ያደረገችውን ሙከራ ከሽፏል” ብለዋል፡፡
የኢራንን ክስ ውድቅ የምታደርገው አሜሪካ በበኩሏ ቴህራን ሰላማዊ ሰልፎችን ለማፈን የሄደችበት ርቅት አውግዛለች፡፡ተቃውሞ “አፍነዋል”ባለቻቸው በሰባት የኢራን ባለስልጣናት ላይም ማዕቀብ መጣሏ የሚታወቅ ነው፡፡