ሩሲያ ከክሄርሶን ወታደሮቿን ማስወጣት ማጠናቀቋን ተናግራለች
ሩሲያ በደቡባዊ ዩክሬን በምትገኘው ክሄርሶን ስልታዊ ከተማ መውጣቷን ያስታወቀች ሲሆን አንድ የክልሉ ባለስልጣን የዩክሬን ሰንደቅ ዓላማ በዋና ከተማዋ መስቀሉን ተናግረዋል።
ሆኖም በርካታ የሩሲያ ወታደሮች ለቀው መውጣት አልቻሉም ብለዋል።
ሮይተርስ የዩክሬን ግስጋሴ ምን ያህል እንደሆነ ማረጋገጥ አልቻልኩም ብሏል። የሩስያ የማፈግፈግ ሁኔታ ወይም የቀሩት የሩሲያ ወታደሮች እጣ ፈንታ ምን እንደሆነም እንዲሁ።
የክሄርሶን የዩክሬን የክልል ም/ቤት አባል ሰርሂ ክላን ብዙ ቁጥር ያላቸው የሩስያ ወታደሮች ስልታዊ ከተማዋን ለማምለጥ ሲሞክሩ ዲንፕሮ ወንዝ መስመጣቸውን እና ሌሎች ደግሞ ሲቪል ልብስ ቀይረው ለመደበቅ እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል።
ከተማዋ በዩክሬን ሃይሎች ቁጥጥር ስር ከሞላ ጎደል ገብታለች ማለት ይቻላል ሲል የም/ቤቱ አባል ተናግረዋል።
ቀደም ሲል የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ኬርሰን ከምትገኝበት ከዲኒፕሮ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻ ወታደሮቹን ማስወጣቱን ተናግሯል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ከጠቀለሏቸው አራት ግዛቶች የክሄርሶን ግዛት አንዱ ነው።
የግዛቱ ዋና ከተማ መልቀቅ በአንዳንድ ሩሲያውያን የዩክሬንን ጥቁር ባህር ዳርቻ የመንጠቅ ህልሞችን የሚያበቃ ይመስላል ብሏል ሮይተርስ።
ሆኖም የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ክልሉ ወደ ሩሲያ መጠቅለል እንዳልተለወጠ ተናግረዋል ።