የስፔኗ ባርሴሎና ነዋሪዎች ጎብኚዎች እንዳይመጡባቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ
ባርሴሎና በዓመት 32 ሚሊዮን ጎብኚዎች የሚጎበኟት ከተማ ነች
በጎብኚዎች መጥለቅለቅ ምክንያት ህይወታችን አሰልቺ ሆኗል ያሉ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል
የስፔኗ ባርሴሎና ነዋሪዎች ጎብኚዎች እንዳይመጡባቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ፡፡
በደቡባዊ አውሮፓ የምትገኘው የስፔኗ ባርሴሎና በጎብኚዎች ከሚዘወተሩ ከተሞች መካከል ዋነኛዋ ናት፡፡
ወቅቱ ክረምት መሆኑን ተከትሎ ከመላው ዓለም ያሉ ጎብኚዎች ወደ ባርሴሎና እንደሚጎርፉ ይጠበቃል፡፡
በአጠቃላይ ባርሴሎና በየዓመቱ በአማካኝ በ32 ሚሊዮን ጎብኚዎች የምትጎበኝ ሲሆን የከተማዋ ነዋሪዎች ጎብኚ በዛብን በሚል በምሬት ላይ እንደሆኑ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ባርሴሎና ብቻ ሳትሆን በካታሎኒያ ግዛት ስር ያሉ ሌሎች ከተሞችም ሰላማዊ ሰልፉን ተቀላቅለዋል፡፡
ሜሲ በ13 አመቱ ለባርሴሎና የፈረመባት ናፕኪን (ሶፍት) ለጨረታ ቀረበች
በባርሴሎና ከተማ እና አቅራቢያ ያሉ ነዋሪዎች ግርግር የሞላበት ህይወት ሰለቸን ጎብኚዎች አይምጡብን ሲሉ በሰላማዊ ሰልፋቸው ላይ ጠይቀዋል፡፡
እንዲሁም ጎብኚዎች የመኖሪያ ቤት እና ሆቴሎች ዋጋን እያናሩብን ላልተገባ የኑሮ ውድነት ዳርገውናል ሲሉም በሰልፉ ላይ መልዕክታቸውን እንዳስተላለፉ ተገልጿል፡፡
ባርሴሎና በዓመት ከምታገኘው ገቢ ውስጥ 14 በመቶ የሚሆነው ከጎብኚዎች ይገኛል የተባለ ሲሆን 10 በመቶ የከተማዋ ነዋሪዎች በቱሪዝም ዘርፍ ተሰማርተዋል ተብሏል፡፡
በርካታ ሀገራት በጎብኚዎች እጥረት ሲመቱ ባርሴሎና እና በአቅራቢያው ያሉ ሌሎች ከተሞች ደግሞ ጎብኚዎች አይምጡብን ማለታቸው ግርምትን አጭሯል፡፡