በሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ግድያ የተጠረጠሩ አንድ ሱዳናዊና ሁለት የውጭ ዜጎች ተያዙ
በሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ግድያ የተጠረጠሩ አንድ ሱዳናዊና ሁለት የውጭ ዜጎች ተያዙ
የሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስትር ፈይሰል ሙሃመድ ሷሊህ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የግድያ ሙከራ ጋር በተያያዘ አንድ ሱዳናዊ እና ሁለት የውጭ ሃገር ዜጎች በድምሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡
ሁለቱ የውጭ ሀገር ተጠርጣሪዎች አረቦች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ ከተካሄደው የሃገሪቱ ካቢኔ ስብሰባ በኋላ በሰጡት መግለጫ የጥቃቱን ፈጻሚዎች ለመለየት የሃገሪቱ ደህንነት የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዙ የአሜሪካ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ.ቢ.አይ) ቡድን አባላት ጠዋት ካርቱም መድረሳቸውን አስታውቀዋል፡፡
ወደ ሀገሪቱ የገቡት 3 የኤፍ.ቢ.አይ አባላት በዋናነት የድርጊቱን አቀናባሪዎች የመለየት ስራ እንደሚያከናውኑ ነው ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ የጠቆሙት፡፡
ከግድያ ሙከራው ጋር በተያያዘ ምንጮች ለ አል-ዐይን እንደገለጹት በድርጊቱ የሱዳን ደህንነት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ከትናንት በስቲያ የካቲት 30 ቀን 2012 ነበር በካርቱም የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው፡፡ የግድያ ሙከራው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መወገዙ ይታወቃል፡፡