ቲክ ቶክ ለአጫጭር ቪዲዮ አዘጋጆች ክፍያ መፈጸም የጀመረባቸው አዳዲስ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የአጫጭር ቪዲዮ ኔትወርክ የሆነው ቲክ ቶክ የቪዲዮ አዘጋጆች የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ በሞዴሉ ላይ ማሻሻያ ማድረጉንም ገልጿል

ተደራሽነቱን እያስፋፋ ያለው ቲክ ቶክ በተጨማሪ አዳዲስ 32 ሀገራት ውስጥ ላሉ የአጫጭር ቪዲዮ አዘጋጆች ክፍያ መፈጸም ሊጀምር ነው ተብሏል
ተደራሽነቱን እያስፋፋ ያለው ቲክ ቶክ በተጨማሪ አዳዲስ 32 ሀገራት ውስጥ ላሉ የአጫጭር ቪዲዮ አዘጋጆች ክፍያ መፈጸም ሊጀምር ነው ተብሏል።
የአጫጭር ቪዲዮ ኔትወርክ የሆነው ቲክ ቶክ የቪዲዮ አዘጋጆች የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ በሞዴሉ ላይ ማሻሻያ ማድረጉንም ገልጿል።
ቴክ ቶክ እንዳስታወቀው አሁን ላይ ሳኡዲ አረቢያን፣ ኩየትን፣ ግብጽን፣ኳታርን፣ ባህሬንን እና ኦማንን ጨምሮ በበርካታ የአረብ ሀገራት ውስጥ ለአጫጭር ቪዲዮ አዘጋጆች ክፍያ መፈጸም ጀምሯል።
ከዚህ በተጨማሪም ቤልጄም፣ ቤላሩስ፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ቼክ፣ ዴንማርክ፣ ኢኳዶር፣ ግሪክ፣ ካዛኪስታን፣ ሜክሲኮ፣ ሞሮኮ፣ ኒውዝላንድ፣ ኖርዌይ፣ ፔሩ፣ ፖርቹጋል፣ ሮማንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስዊድን፣ ኦስትሪያ፣ ታይዋን፣ ቱርክ እና ኡራጓይ ቲክ ቶክ ክፍያ መፈጸም ከጀመረባቸው ሀገራት ውስጥ ይገኙበታል።
የእነዚህ ሀገራት መካተት ቲክ ቶክ ለአጫጭር ቪዲዮ አዘጋጆች ክፍያ የሚፈጽምባቸውን ሀገራት ወደ 53 ሀገራት ከፍ እንዲል አድርጎታል።
ንብረትነቱ የቻይናው ባይቲዳንስ የሆነው ቲክ ቶክ እንደገለጸው የክፍያ መርሀግሩ ከተጀመረ ከባለፈው አመት ጀምሮ ጥቂት አዘጋጇች በአንድ ቨዲዮ እስከ 14ሺ ዶላር ያገኙ ሲሆን በወር ደግሞ 50 ዶላር ማግኘት ችለዋል።
አዘጋጆችን ለማበረታት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ክፍያውን በ250 በመቶ ከፍ ማድረጉን ቲክ ቶክ ገልጿል።
ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ቲክ ቶክ የደንበኞችን መረጃ ለቻይና መንግስት ይሰጣል የሚሉ አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በቲክ ቶክ ላይ ሙሉ በሙሉ እግድ ጥለዋል።
አሜሪካ በርካታ ግዛቶች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ቲክ ቶክን እንዳይጠቀሙ እግድ የጣለች ሲሆን በቅርቡ ደግሞ በሀገር ደረጃ እንድ እንድትጥል ረቃቅ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል።