ቲክቶክ የድመፅ የቀጥታ ስርጭትን ጨምሮ ሌሎችንም አገልግሎቶች ይፋ ሊያደርግ ነው ተባለ
ቲክቶክ እየሰራባቸው ካሉ አዳዲስ አገልግቶች ውስጥ ‘ቢትሞጂ’ የተባለ በራሳችን ምስል የሚሰራ ኢሞጂ አንዱ ነው
የቡድን የመልክት መላላኪያ (ግሩፕ ቻት) ቲክቶክ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ከሚጠበቅ አገልግሎት ውስጥ ነው
የአጫጭር ተንቀሳቃሽ ምስሎች (ቪዲዮዎች) ማጋሪያ የሆነው ቲክቶክ በርካታ ተጠቃሚዎችን እያፈሩ ካሉ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ውስጥ አንዱ እየሆነ መጥቷል።
ታዲያ ይህ የማህበራዊ ትስስር ገፅ አዳዲስ አገልግሎቶችን ይዞ ለመምጣት በሙከራ ደረጃ እየሰራ መሆኑን ቴክ ክረንች የተባለው በቴክኖሎሎ ዙሪያ ዘገባዎችን የሚያቀርብ ድረ ገፅ አስነብቧል።
ቲክቶክ እየሰራባቸው ካሉ አዳዲስ አገልግቶች ውስጥ ‘ቢትሞጂ’ የተባለ በራሳችን ምስል የሚሰራ ኢሞጂ (አሻንጉሊት ምስል) አንዱ ነው ተብሏል።
ቲክቶክ አቫተር የሚል መጠሪያ የተሰጠውን ይህንን አዲሱን አገልግሎት ለማግኘትም የስልካችን የፊትለፊት (ሰልፊ) ካሜራ በመጠቀም ራሳችንን ፎቶ ካነሳን በኋላ ምስላችንን ከምንፈልገው አሻንጉሊት ጋር እንዲዋሃድ በማድረግ መጠቀም የሚያስችል ነው።
ቲክቶክ ሌላው እየሰራበት ያለው አዲሱ አገልግሎት የቡድን የመልክት መላላኪያ (ግሩፕ ቻት) መሆኑን ከኩባያው አፈትለከው የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የድምጽ ብቻ ቀጥታ ስርጭት (audio-only livestreams) ቲክቶክ በቀርቡ ይፋ ያደርገዋል ተብሎ ከሚጠበቅ አገልግሎቶቹ ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ይህም ያለ መስል በድምጽ ብቻ ቀጥታ ስርጭት ለማድረግ የሚያስችል መሆኑም ታውቋል።
ሌላው የቲክቶክ አዲስ አገልግሎት በቪዲዮ ቀጥታ ስርጭት ወቅት የራሳችንን የስልክ ስክሪን ለሌሎች ማጋረት የሚያስችል እንደሆነም ተጠቁሟል።
ቲክቶክ አዳዲሶቹን አገልግሎቶች አሁን ባለው መተግበሪያ አሊያም በሌላ ፕላትፎርም ይዞ ሊመጣ ይችላል የሚለውም እየተነገረ ነው።
የቲክቶክ ኩብንያ ቃል አቀባይ ለቴክ ክረንች እንደተናገሩት፤ ሁሌም አዲስ ነገር ይዘን ለመምጣት ነው የምንሰራው፤ አሁን አፈትልከው የወጡ የቲክቶክ አገልግሎቶች ወደ ፊት ሙሉ በሙሉ ለምተው ሊለቀቁ አሁን ካለው የበለጠ ልዩነት ሊፈጥር ይችላል ብለዋል።
ከአዳዲሶቹ አገልግሎቶች ውስጥም የተወሰኑት ላይ ሙከራ መደረጉንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።