ቲክቶክ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል ቃል ገባ
ኩባንያው የሀቅ ፍተሻ መርሀ-ግብሩን በመላው አውሮፓ የቋንቋ ሽፋንን በመጨመር ያስፋፋል ተብሏል
ቲክ ቶክ ባለፉት ስድስት ወራት የማስታወቂያ ፖሊሲውን የጣሱ 191 ማስታወቂያዎችን አስወግጃለሁ አለ
ቲክቶክ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል ቃል ገባ።
የቻይና የተንቀሳቃሽ ምስል ማጋሪያ ኩባንያ ቲክቶክ በዩክሬን እየተካሄደ ካለው ጦርነት በመነሳሳት ተጨማሪ የደህንነት ባህሪያትን በመጨመርና የእውነታ ማረጋገጫ እርምጃዎችን በማስፋት በመድረኩ ላይ ሀሰተኛ መረጃን ለመቅረፍ ቃል ገብቷል ።
ኩባንያው ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በሀሰተኛ መረጃ ላይ የአውሮፓ ህብረት የተጠናከረ መመሪያን ለማሟላት የተጓዘበትን ሂደት ሪፖርት ማድረጉን ሮይተርስ ዘግቧል።
በዚህም ኩባንያው ጥረቱን ማጠናከር እንዳለበት አምኗል ነው የተባለው።
"ይህንን የዝርዝር ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በማቅረባችን ኩራት ቢሰማንም ብዙ የሚጠብቀን ስራ እንዳለ እንገነዘባለን። በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ በርካታ ተነሳሽነት እናደርጋለን" ስሉ ካሮሊን ግሬር የህዝብ ፖሊሲና የመንግስት ግንኙነት ኃላፊዋ ተናግረዋል።
ኃላፊዋ ቲክ ቶክ መንግስት የሚቆጣጠራቸው የሚዲያ መለያዎችን ልየታ ያሰፋል፣ ከዩክሬን ጋር በተገናኘ የሀሰት መረጃ ላይ እርምጃን ያጠናክራል፣ የሀቅ ፍተሻ መርሀ-ግብሩን በመላው አውሮፓ በማስፋፋት የቋንቋ ሽፋንን ይጨምራል፣ በእውነት ላይ የተረጋገጠ የይገባኛል ጥያቄ መጠን ይጨምራል በማለት ቀጣይ እርምጃዎችን ተናግረዋል።
ኩባንያው በማስታወቂያ ፓሊሲው ውስጥ የሀሰተኛ መረጃ አቀራረቡን ያጠናክራልም ተብሏል።
ቲክ ቶክ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የፖለቲካ ማስታወቂያ እገዳውን የጣሱ የተለያየ ይዘት ያላቸው 191 ማስታወቂያዎችን ማስወገዱን አስታውቋል።