የቶክዮ ኦሎምፒክ የሜዳሊያ ሰንጠረዥን እየመሩ ያሉ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
በዘንድሮው የቶክዮ ኦሎምፒክ ላይ ለሚያሸንፉ ስፖርተኞች 5 ሺህ ሜዳሊያዎች ለሽልማት ተዘጋጅተዋል
እስካሁን 52 ሀገራት የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት መቻላቸው ተነግሯል
በጃፓን አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 32ኛው የ2020 የቶክዮ ኦሎምፒክ ከተጀመረ ዛሬ 5ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
የቶክዮ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች መጀመሩን ተከትሎም በርካታ ውድድሮች ፍጻሜ አያገኙ ሲሆን፤ በርካታ ሀገራም የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት ጀምረዋል።
በዚህም መሰረት ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ጃፓን የሜዳሊያ ሰንጠረዡን በ10 የወርቅ፣ 3 የብር እና 5 የነሃስ በድምሩ በ18 ሜዳሊያዎች በመምራት ላይ ትገኛለች።
አሜሪካ ደግሞ በ9 የወርቅ እና በ7 የብር እና 8 የነሃስ በድምሩ በ24 ሜዳሊያዎች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፤ ቻይና በ9 የወርቅ፣ 5 የብር እና 7 የነሃስ በድምሩ በ21 ሜዳሊያዎች 3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ሩሲያ በ7 የወርቅ፣ 7 የብር እና 4 የነሃስ ሜዳሊያዎች 4ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፤ ብሪታንያ ደግሞ በ4 የወርቅ፣ 5 የብር እና 4 የነሃስ ሜዳሊያዎች 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ደቡብ ኮሪያ፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ እና ኮሶቮ ደግሞ ደግሞ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ከ6ኛ እስከ 10ኛ ደረጃ ያለውን ይዘዋል።
እስካሁን ባለው መረጃም 52 ሀገራት የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት መቻላቸውን ከስፍራው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
በዘንድሮው የ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ከ205 ሀገራት የተውጣቱ ከ11 ሺህ በላይ አትሌቶች እንደሚሳተፉ ከስፍራው ተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ 33 አይነት ስፖርታው ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ በውድድሩ ለሚያሸንፉ አትሌቶችም 5 ሺህ ሜዳሊያዎች ለሽልማት ተዘጋጅተዋል።