ራሰ በራነት የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ስፔን ጣልያን እና ፈረንሳይ ራሰ በራ የሆኑ ወንዶች የበዛባቸው ሀገራት ናቸው
ከአፍሪካ ደቡብ አፍሪካ እና ግብጽ በአንጻራዊነት ራሰ በራነት የተስፋፋባቸው ሀገራት ናቸው
ራሰ በራነት የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ሜድ ሀይር የተሰኘው የጸጉር ጤንነት እና ጥናት ተቋም በራሰ በራነት ዙሪያ ያወጣውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
እንደ ድርጅቱ 2024 ሪፖርት ከሆነ አውሮፓዊያን እና ሰሜን አሜሪካ አህጉራት ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲነጻጸሩ የበለጠ ለራሰ በራነት ተጋልጠዋል፡፡
በቂ የጸሀይ ብርሃን አለመኖር፣ የተቀነባበሩ ምግቦችን ማዘውተር እና ድብርት ለጸጉር መመለጥ ወይም ራሰ በራነት እንደሚያጋልጡ ተገልጿል፡፡
በዚህ ሪፖርት መሰረት ስፔን 44 በመቶ ወንዶቿ ራሰ በራ ሲሆኑ ጣልያን እና ፈረንሳይም በተመሳሳይ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
ከአፍሪካ ደቡብ አፍሪካ እና ግብጽ ሁለተኛ እና ሶስትኛ ሲሆኑ ከዓለም ደግሞ በ34ኛ እና እና 36ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡
ራሰ በራነት አንድ የውበት መገለጫ ሲሆን ብዙዎች ፈልገውም ሆነ ሳይፈልጉ ራሰ በራነትን የሚከተሉ ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡
በአውሮፓ የሚገኘው ካውካሺያን የተሰኘው የሰው ዘር በሌላ አህጉር ከሚኖረው የበለጠ ለራሰ በራነት የተጋለጠ እንደሆነ ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው ሪፖርት ያስረዳል፡፡