በ2022 የስማርት ስልኮች ቁጥር ከአለም ህዝብ ቁጥር መብለጡ የሚታወስ ነው
በያዝነው የፈረንጆቹ አመት የስማርት ስልክ ባለቤት የሆኑ ሰዎች ቁጥር 4.88 ቢሊየን ደርሷል።
ይህም ካለፈው አመት የ635 ሚሊየን ብልጫ አለው የሚለው ስታቲስታ፥ ከ2020 ወዲህ ባሉት አራት አመታት 2.61 ቢሊየን ሰዎች ስማርት ስልኮችን መጠቀም መጀመራቸውን ይገልጻል።
በቀጣይ አምስት አመታትም 1.5 ቢሊየን ሰዎች የየእለት ህይወትን የሚያቀላጥፉትን ስልኮች ሸምተው በ2029 6.4 ቢሊየን የአለማችን ህዝብ የስማርት ስልክ ባለቤት እንደሚሆን ይገመታል።
የአለማቀፉ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ማህበር የስማርት ስልክ ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ከአለማችን ህዝብ የበለጠው በ2022 ነበር።
በወቅቱ የአለም ህዝብ ቁጥር 7.95 ቢሊየን የነበረ ሲሆን፥ በተጠቃሚዎች እጅ የገቡ ስማርት ስልኮች ቁጥር ግን 8.58 ቢሊየን ነበር።
በ2024 መጨረሻ ስማርት ስልኮች ያሏቸው ሰዎች ቁጥር 5 ቢሊየን ደርሷል ቢባልም፥ ለሽያጭ የቀረቡት ስልኮች ቁጥር ግን 7 ነጥብ 21 ቢሊየን ደርሷል ይላል ባንክማይሴል የተባለ የስማርት ስልኮችን ሽያጭ የሚከታተል ድረገጽ። ከአንድ በላይ ስማርት ስልክ ያላቸው ተጠቃሚዎች መኖራቸውንም በማውሳት።
ቀጥሎ በርካታ ስማርት ስልክ ተጠቃሚ ዜጋ ያላቸውን ሀገራት ይመልከቱ፦