ከፍተኛ የወንዶች ህዝብ ብዛት ያለባቸው የዓለማችን ሀገራት
የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሴቶች ቁጥር አነስተኛ ከሆኑባቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚ ሆነዋል
ሲሸልስ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ደግሞ ከአፍሪካ በወንዶች ቁጥር ቀዳሚ የሆኑ ሀገራት ናቸው
ከፍተኛ የወንዶች ህዝብ ብዛት ያለባቸው የዓለማችን ሀገራት
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ፖሊሲ ሪፖርት ከሆነ በዓለማችን ካለው 8 ቢሊዮን ጠቅላላ ህዝብ ውስጥ ወንዶች ከሴቶች በ40 ሚሊዮን ብልጫ አላቸው፡፡
ይሁንና በተወሰኑ የዓለማችን ሀገራት ደግሞ የጾታ አለመመጣጠን ያለ ሲሆን በተለይም በመካከለኛው መስራቅ ሀገራት ወንዶች ከሴቶች ያላቸው ልዩነት የሰፋ ሆኗል፡፡
ኳታር፣ ባህሬን እና የተባበሩት አረብ ኢምሬት የወንዶች ቁጥር ከሴቶቹ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ልዩነት ያለው ሲሆን ለነዚህ ሀገራት የጾታ አለመመጣጠን ዋነኛው ምክንያት ለስራ በሚል ከተለያዩ ሀገራው የሚገቡ ወንዶች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ እንደሆነ ዓለም አቀፉ የህዝብ ፖሊሲ ጥናት ሪፖርት ያሳያል፡፡
ከአፍሪካ ኢኳቶሪያ ጊኒ እና ሲሸልስ ከፍተኛ የወንዶች ብዛት ያለባቸው ሀገራት ሲሆኑ አርመንያ፣ ዩክሬን፣ ቤላሩስ፣ ላቲቪያ፣ ዚምባብዌ እና ሩሲያ ደግሞ በተቃራኒው የሴቶች ህዝብ ብዛት ከፍተኛ የሆኑባቸው ሀገራት ናቸው፡፡