የዓለማችን ቀዳሚ ስደተኛ ተቀባይ ሀገራት እነማን ናቸው?
አሜሪካ 50 ሚሊዮን ስደተኞችን በመያዝ ዓለማችን ቀዳሚዋ ሀገር ናት
ጀርመን እና ሳውዲ አረቢያ ከአሜሪካ በመቀጠል ስደተኞች ከሚኖሩባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
የዓለማችን ቀዳሚ ስደተኛ ተቀባይ ሀገራት እነማን ናቸው?
የሰው ልጅ ከሀገር ወደ ሀገር መሰደድ ተፈጥሯዊ ፍላጎት ሲሆን የተሻለ ምቾት ፍለጋ፣ የደህንነት ስጋት እና ድህነት ደግሞ ለሰው ልጆች መሰደድ ዋነኛ ገፊ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ሀገራት ይህንን የሰው ልጆች የመሰደድ ተፈጥሯዊ ፍላጎት መነሻ በማድረግ እና ከዚህ ለመጠቀም ህግ እና ስርዓት ቀርጸዋል፡፡
ለአብነትም አሜሪካ ስደተኞችን በመጠቀም ኢኮኖሚዋን በመደጎም ከሚታወቁ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ስትሆን ስደተኞች አዳዲስ ፈጠራዎችን ጨምሮ ሀገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟን ያስጠሩ ስኬቶችን አስመዝግባለች፡፡
ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ በአውሮፓ ካሉ ሰራተኞች ውስጥ 70 በመቶው ስደተኞች ሲሆኑ በአሜሪካ ደግሞ 47 በመቶ ድርሻ አላቸው፡፡
ከአሜሪካ አጠቃላይ ህዝብ ውስጥ 50 ሚሊዮን ያህሉ ስደተኞች ሲሆኑ ጀርመን 16 ሚሊዮን፣ ሳውዲ አረቢያ 13 ሚሊዮን እንዲሁም ሩሲያ 11 ሚሊዮን ሰዎች ስደተኞች መሆናቸውን ወርልድ ፖፑሌሽን ያስጠናው ጥናት ያስረዳል፡፡