ቦትስዋና፣ ሩሲያ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ የዓለማችን ቀዳሚ የዳይመንድ አምራቾች ናቸው
የዓለማችን ምርጥ 10 ዳይመንድ አምራች ሀገራት
ዳይመንድ ወይም አልማዝ ማዕድን በውስን ዓለማችን ሀገራት የሚመረት ውድ ማዕድን ሲሆን በዓመት እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር ግብይት ይፈጸምበታል፡፡
አፍሪካ በዚህ ማዕድን የተትረፈረፈ ሀብት ቢኖራትም የዓለም ገበያን የተቆጣጠሩት ግን ጥሬ ማዕድኑን በመግዛት እና የተወሰነ እሴት የሚጨምሩ ሀገራት ናቸው፡፡
ቦትስዋና የዓለማችን ዋነኛ የዳይመንድ አምራች ሀገር ስትሆን አውሮፓዊቷ ሩሲያ ሁለተኛ እንዲሁም ዲሞክራቲክ ኮንጎ ደግሞ ሶስተኛዋ አምራች ሀገር ናት፡፡
በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ 10 ዳይመንድ አምራች ሀገራት ውስጥ ዘጠኙ አፍሪካዊ ሲሆኑ በተለይም ደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የማዕድኑ ዋነኛ መገኛ ሀገራት ናቸው፡፡