የእስያ ሀገራት የዓለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠው አማካኝ የዓለም አየር ብክለት ደረጃ ከ10 እጥፍ በላይ ናቸው ተብሏል
ከፍተኛ የአየር ብክለት ያለባቸው ዓለማችን ከተሞች
ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ በሽታዎች በዓለማችን ካሉ የሞት መንስኤዎች መካከል በገዳይነታቸው ሶስተኛ ደረጃ ለይ እንደሚገኙ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያስረዳል፡፡
ለኑሮ ተስማሚ ያልሆነ አየር አለመገኘት ደግሞ ለመተንፈሻ አካላት ህመም መነሻ ሲሆን የእስያ ሀገራት ከሌሎቹ አህጉራት የከፉ እንደሆኑም ተገልጿል፡፡
ባንግላዲሽ፣ ህንድ እና ፓኪስታን በዓለማችን ከፍተኛ የአየር ብክለት ካለባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት አማካኝ የአየር ብክለት ብሎ ካስቀመጠው 10 እጥፍ የባሱ ናቸው ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ከአፍሪካ ቡርኪናፋሶ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ በተመሳሳይ የከፋ አየር ብክለት ያለባቸው ሀገራት ሲባሉ ኢራቅ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት እና ኩዌትም በአንጻራዊነት የከፋ የአየር ብክለት ያለባቸው ሀገራት እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡