አረብ ኢምሬትስ በ2050 ከኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚመነጭ ብክለትን 93 በመቶ ለመቀነስ አቀደች
አረብ ኢምሬትስ በ2050 ብሄራዊ የካርበን ነጻ ግብን ለማሳካት ፍኖተ ካርታውን ከስትራቴጂክ አጋሮቿ ጋር በመሆን አዘጋጅታለች
ሀገሪቱ ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችል 'በኢንዱስትሪ ሴክተር ያለውን የካርቦን ልቀት የሚቀንስ ፍኖተ ካርታ' አስጀምራለች
አረብ ኢምሬትስ በ2050 ከኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚመነጭ ብክለትን 93 በመቶ ለመቀነስ አቀደች።
የኮፕ28 የአየር ንብረት ስብሰባ እያስተናገደችው ያለችው አረብ ኢምሬትስ በ2050 የኢንዱርትሪው ዘርፍ የሚያደርሰውን ብክለት 93 በመቶ ለመቀነስ ማቀዷን አስታውቃለች።
ሀገሪቱ ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችል 'በኢንዱስትሪ ሴክተር ያለውን የካርቦን ልቀት የሚቀንስ ፍኖተ ካርታ' አስጀምራለች፡
አረብ ኢምሬትስ ይህን ያደረገችው የአየር ንብረት የሚያስከትለውን ችግር ለመጋፈጥ ቁርጠኛ በመሆኗ ነው ተብሏል። ይህ እርምጃ ብሄራዊ ዘላቂ ልማትን ለማምጣትም ያስችላል ተብሏል።
የኢምሬትስ ኒውስ ኤጀንሲ እንደዘገበው አረብ ኢምሬትስ በ2050 ብሄራዊ የካርበን ነጻ ግብን ለማሳካት ፍኖተ ካርታውን ከስትራቴጂክ አጋሮቿ ጋር በመሆን አዘጋጅታለች።
ፍኖተ ካርታው በ2050፣ 93 በመቶ ብክለትን ከመቀስ በፊት በ2030፣ 5 በመቶ እና በ2040፣ 63 በመቶ ለመቀነስ እቅድ መያዙን ጠቅሷል።