
በጤና ተስማሚነቱ ተፈላጊ እየሆነ የመጣው ጤፍ አሜሪካ እና ሕንድን ጨምሮ በተለያዩ አህጉራት መመረት ጀምሯል
ጤፍ የሚያመርቱ የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎች ለዘመናት ሲያመርቱት የቆየው ጤፍ ባህር ማዶ ተሸግሮ መመረት ጀምሯል ተብሏል፡፡
ከኢትዮጵያዊን ማዕድ ላይ የማይጠፋው ጤፍ አነስተኛ የስኳር መጠን መያዙ፣ ከሌሎች ምግቦች ጋር መቀላቀል እና መመገብ የሚቻል መሆኑ ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የዓለም የምግብ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ ዋነኛ የጤፍ አምራች ሀገር ስትሆን ኡጋንዳ ሁለተኛዋ ጤፍ አምራች ሀገር ናት፡፡
ኤርትራ፣ ሱዳን፣ አሜሪካ፣ ሕንድ፣ ካናዳ፣ ኒውዝላንድ እና ሆላንድ ጠየፍ ከሚያመርቱ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ከአፍሪካ ውጪ ጤፍ ከሚመረትባቸው አህጉራት መካከል አውሮፓ፣ እስያ እና ሰሜን አሜሪካ ዋነኞቹ ናቸው