የጉበት በሽታ የተስፋፋባቸው ሀገራት እነማን ናቸው?
ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 ሀገራት በዓለም ካለው የቫይረሱ ተጠቂዎች አብዛኛውን ድርሻ ይይዛሉ ተብሏል
በዓለም ላይ ከሚወለዱ ህጻናት ውስጥ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት የሚወስደው አንዱ ብቻ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል
የጉበት በሽታ የተስፋፋባቸው ሀገራት እነማን ናቸው?
የዓለም ጤና ድርጅት ከሰሞኑ ትኩረቱን በጉበት በሽታ ዙሪያ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ የዓለም ጉበት በሽታ ስርጭት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በተለይም በሄፓታጥቲስ ቢ የሚጠቁ ዜጎች ቁጥር መጨመሩን አስታውቋል፡፡
በዓለማችን በየዕለቱ 3 ሺህ 500 ሰዎች በጉበት በሽታ እየሞቱ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በጉበት በሽታ ከሚሞቱት ውስጥም 83 በመቶዎቹ በሄፓታይተስ ቢ በተሰኘው የጉበት በሽታ የሚሞቱ ናቸው ተብሏል፡፡
በጉበት በሽታ የሚጠቁ ዜጎች እየጨመረ ነው ያሉት ሃላፊው 63 በመቶ ያህሉ ተጠቂዎች በአፍሪካ የሚገኙ ዜጎች እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡
ይህ በሽታ እየተሰራጨባቸው ካሉ 10 ሀገራት መካከልም ኢትዮጵያ አንዷ ናት የተባለ ሲሆን ባንግላዲሽ፣ ቻይና፣ ሕንድ እና ሌሎችም ሀገራት ተጠቅሰዋል፡፡