ከ94 ዓመት በፊት በተጀመረው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያ 11 ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ተጫውታለች
በፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር 1930 ላይ የተጀመረው የዓለም ዋንጫ 22 ጊዜ ተካሂዷል፡፡
ውድድሩ ከተጀመረ ጀምሮ 80 ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ100 በላይ ሀገራት አንድም ጊዜ አልተሳተፉም፡፡
ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች ብቻ ዋንጫ የበሉበት ይህ የዓለም ዋንጫ ውድድር አንድ ክፍለ ዘመን ሊሆነው አምስት ዓመታት ብቻ ቀርተውታል፡፡
100 ሚሊዮን እና ከዛ በላይ ህዝብ ካላቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ሕንድ፣ ፓኪስታን፣ አፍጋኒስታን እና ፊሊፒንስ ለዓለም ዋንጫ አልፈው አያውቁም፡፡
በ2026 በአሜሪካ፣ሜክሲኮ እና ካናዳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ሀገራት የማጣሪያ ጨዋታዎችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡