ቻይና እና ሩሲያ ከፍተኛ በጀት ለመከላከያ ካወጡ ሀገራት መካከል ናቸው
ከፍተኛ ወታደራዊ በጀት የመደቡ የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
የፈረንጆቹ 2023 ዓመት በታሪክ ከፍተኛ ገንዘብ ለወታደራዊ ተቋማት ወጪ ከተደረገባቸው ዓመታት ውስጥ አንዱ ሆኗል፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል የሆነችው አሜሪካ 961 ቢሊዮን ዶላር ለወታደራዊ ጉዳዮች ወጪ አድርጋለች የተባለ ሲሆን ቻይና 296 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ሩሲያ ደግሞ 109 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርጋለች ተብሏል፡፡
ሌላኛዋ የሩቅ ምስራቅ ሀገር ሕንድ 83 ቢሊዮን ዶላር ለመከላከያ ወጪ ስታርግ ሳውዲ አረቢያ 76 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ናይትድ ኪንግደም ደግሞ 75 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንዳደረገች ተገልጿል፡፡
ጀርመን 66 ቢሊዮን ዶላር፣ ከሩሲያ ጋር እየተዋጋች ያለችው ዩክሬን 65 ቢሊዮን ዶላር ስታደርግ ፈረንሳይ 61 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ጃፓን ደግሞ 50 ቢሊዮን ዶላር ለመከላከያ ሰራዊት ወጪ ካደረጉ የዓለማችን 10 ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡