የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በነዳጅ ሀብታቸው ከበለጸጉ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
10ሩ የዓለማችን ነዳጅ ሀብታም ሀገራት እነማን ናቸው?
ዓለም አቀፉ የነዳጅ ላኪ ሀገራት ባወጣው መረጃ መሰረት ቬንዙዌላ ባላት ነዳጅ ሀብት የዓለማችን የነዳጅ ሀብታም ሀገር ስትሆን ሳውዲ አረቢያ እና ካናዳ ደግሞ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሀገራት ናቸው፡፡
ኢራን፣ ኢራቅ እና ኩዌት ደግሞ በቅደም ተከተላቸው መሰረት ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ደረጃ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
በነዳጅ ሀብቷ 10 ደረጃ ላይ የምትገኘው አሜሪካ ከ2018 ጀምሮ የዓለማችን ቀዳሚዋ ነዳጅ አምራች ሀገር ስትሆን በ2022 ላይ ብቻ በየቀኑ በአማካኝ 18 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ አምርታ ለገበያ አቅርባለች፡፡
ቬንዙዌላ እና ኢራን ከፍተኛ የኘዳጅ ሀብት ያላቸው ሀገራት ቢሆኑም በአሜሪካ ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ ነዳጃቸውን እንደልብ ለዓለም ገበያ ማቅረብ አልቻሉም፡፡
ሳውዲ አረቢያ በ2022 ዓመት ብቻ 311 ቢሊዮን ዶላር ከነዳጅ ሽያጭ ገቢ ማግኘቷ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ የነዳጅ ሀብት ካላቸው ዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን 428 ሺህ በርሜል ነዳጅ ሀብት በመያዝ 98ኛዋ ሀገር ተብላለች፡፡