በዩኔስኮ በርካታ ቅርሶችን ያስመዘገቡ ሀገራት
የመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በ168 ሀገራት 1 ሺህ 199 ቅርሶችን የአለም ቅርስ አድርጎ መዝግቧል
ጣሊያን፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን በርካታ ቅርሶችን በማስመዝገብ ቀዳሚዎቹ ሀገራት ናቸው
የመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ከሁለቱ የአለም ጦርነቶች በኋላ በ1945 ነው የተቋቋመው።
የጦርነቱ ተፋላሚዎች የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸውን የሚያጠናክሩና ዘላቂ ሰላምን ማስፈን የሚያስችሉ ስምምነቶችን መፈራረማቸው በቂ አይደለም ብሎ የተነሳው ዩኔስኮ፥ መላው አለምን በሚያስተሳስሩና የጋራ መግባባት በሚፈጥሩ ቅርሶች ላይ ሲሰራ ቆይቷል።
በፈረንጆቹ 1972ም የአለም ቅርስ ኮንቬንሽንን አውጥቶ የሰው ልጅ ድንቅ የጥበብ ውጤት የሆኑ፣ ድንበር ተሻጋሪ ሰው ሰራሽ ወይም ባህላዊ ቅርሶች እና የተፈጥሮ ሃብቶችን በአለም ቅርስነት መመዝገብ ጀምሯል።
ዩኔስኮ ለመጀመሪያ ጊዜ የአለም ቅርስ አድርጎ የመዘገበው በኢኳዶር የሚገኙትን የጋላፓኮስ ደሴቶችና ውብ መልካ ምድር ነበር።
ድርጅቱ እስካሁንም በ168 ሀገራት የሚገኙ 1 ሺህ 199 ቅርሶችን (933 ባህላዊ፣ 227 ተፈጥሯዊ) የአለም ቅርስ አድርጎ መዝግቧል።
ጣሊያን፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን በርካታ ቅርሶችን በማስመዝገብ ቀዳሚዎቹ ሀገራት ናቸው።
ኢትዮጵያም ዘጠኝ ባህላዊ እና ሁለት ተፈጥሯዊ ቅርሶችን በማስመዝገብ 30ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በዩኔስኮ በርካታ ቅርሶች ያስመዘገቡትን ሀገራት ይመልከቱ፦