አሳ በአለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ ከሆኑ የምግብ አይነቶች መካከል አንዱ ነው
በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው የአሳ ምርት ተፈላጊነት እየጨመረ ይገኛል ሀገራት የተለያየ ዝርያ ያላቸውን አሳዎች አምርተው ከራሳቸው አልፎ ለውጭ ገበያ ያቀርባሉ፡፡
አሳ በስፋት ለምግብነት ከሚውልባቸው ሀገራት መካከል በሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ አንድ አሜሪካዊ በአማካይ 14.7 ፓውንድ አሳ ይመገባል፡፡
አሳ ንጹህ የፕሮቲን መገኛ መሆኑን ተከትሎ፣ ከጤና እና ከአዕምሮ እድገት ጋር በተያያዘ ካለው ጠቀሜታ አንጻር በገበታ ላይ እየተዘወተር እንደሚገኝ የሚነግረው የአለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት መረጃ፤
አሳን ጨምሮ ሌሎች የባህር ምግቦችን አቀነባብረው የሚሸጡ ኢንዱስትሪዎች በ2018 31.6 ቢልየን ትርፍ ማግኝታቸውን ጠቁሟል፡፡
በ2017 በአለም አቀፍ የአሳ ምርት ገበያ 125.2 ቢልዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2023 ይህ ቁጥር ወደ 155.3 ቢልዮን ዶላር አድጓል፡፡
ቻይና በአመት 63.8 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በማምረት በአለም ላይ ቀዳሚዋ አሳ አምራች ሀገር ስትሆን ኢንዶኔዢያ 15.6 ህንድ ደግሞ 14.5 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በማምረት በደረጃ ይከተሏታል፡፡