ዩናይትድ ኪንግደም እና ሳውዲ አረቢያ በወታደራዊ ጦር ማዘዣ ብዛት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሀገራት ናቸው
ብዙ ወታደራዊ ማዘዣ ያላቸው የዓለማችን ሀገራት
ሀገራት በዓለም ላይ ያላቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ እና ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለማሳካት ከሌሎች ሀገራት ጋር መስራት የተለመደ ነው።
የዓለማችን ልዕለ ሀያል የሆነችው አሜሪካ ከሀገሯ ውጪ 750 ወታደራዊ ማዘዣዎች አሏት።
ሀገሪቱ ጥቅሞቿን ለማስከበር በሚል ከ170 ሺህ በላይ ወታደሮቿን ወደ ተለያዩ ሀገራት አሰማርታለች።
ከአሜሪካ በመቀጣል ዩናይትድ ኪንግደም 60 ወታደራዊ ማዘዣ በተለያዩ ሀገራት ሲኖራት ሳውዲ አረቢያ፣ ሩሲያ እና ፈረንሳይም ከሀገራቸው ውጪ ብዙ ወታደሮቻቸውን ያሰፈሩ ሀገራት መሆናቸውን የስታስቲካ መረጃ ያስረዳል።