ቱርክ ለእስራኤሉ ሞሳድ መረጃ በመሸጥ የጠረጠረቻቸውን 7 ሰዎች አሰረች
ምንጮቹ እንደሚሉት ከሆነ እሰሩ የቱርክ ብሔራዊ ደህንነት እና የኢስታንቡል ጸረ-ሽብር ፖሊስ የሚያደርገው ዘመቻ አካል ነው
የቱርክ ፍርድ ቤት ባለፈው ጥር ወር ከሞሳድ ጋር ግንኙነት በማድረግ የተጠረጠሩ 15 ሰዎች እንዲታሰሩ እና ሌሎች ስምንት ሰዎች ደግሞ እንዲባረሩ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል
ቱርክ ለእስራኤሉ ሞሳድ መረጃ በመሸጥ የጠረጠረቻቸውን 7 ሰዎች አሰረች።
የቱርክ ፖሊስ ለእስራኤሉ የስለላ ድርድት (ሞሳድ) መረጃ በመሸጥ የጠረጠረቻቸውን ሰባት ሰዎች ማሰሯን ሮይተርስ የቱርክ መገናኛ ብዙኻንን ጠቅሶ ዘግቧል።
ከሰባቱ ተጠርጣሪዎች ውስጥ የቀድሞ የመንግስት ሰራተኛ የሆነው ግለሰብ የመካከለኛው ምስራቅ ኩባንያዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን በመሰብሰብ እና በቱርክ ውስጥ ያሉ ግለሰቦችን የመከታተያ መሳሪያ ገጥሞ በመሰለል መጠርጠሩን የቱርክ የጸጥታ ምንጮች ተናግረዋል።
ምንጮቹ እንደሚሉት ከሆነ እሰሩ የቱርክ ብሔራዊ ደህንነት እና የኢስታንቡል ጸረ-ሽብር ፖሊስ የሚያደርገው ዘመቻ አካል ነው።
በዚህ ዘመቻ ዙሪያ አንካራ በይፋ ያለችው ነገር የለም።
ለሞሳድ በመሰለል የታሰረው ቱርካዊ ግለሰብ በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ ስልጠና መውሰዱን እና በክሪፕቶከረንሲ ክፍያ እንደተፈጸመለት ምንጮቹን ጠቅሶ ዘገባው ጠቅሷል።
የቱርክ ፍርድ ቤት ባለፈው ጥር ወር ከሞሳድ ጋር ግንኙነት በማድረግ እና በፍልስጤም ውስጥ ያሉ ቱርኮችን በመሰለል የተጠረጠሩ 15 ሰዎች እንዲታሰሩ እና ሌሎች ስምንት ሰዎች ደግሞ ከሀገር እንዲባረሩ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።
የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ባለፈው ጥቅምት ወር ከተጀመረ ወዲህ እስራኤል እና ቱርክ ሀይለ ቃል እየተቀያየሩ ናቸው።
ቱርክ፤ እስራኤል ከፍልስጤም ግዛት ውጭ ያሉ የሀማስ አባላትን የምታሳድድ ከሆነ የከፍ ችግር ያጋጥማታል ስትል አስጠንቅቃለች።