ብዙ ዜጎቻቸው በውፍረት የተጠቁባቸው ሀገራት
ውፍረት በዓለማችን ሰዎችን ለሞት ከሚያጋልጡት መካከል ሶስተኛው ነው ተብሏል
ኩዌት፣ አሜሪካ፣ ሊቢያ ብዙ ዜጎቻቸው በውፍረት ሲጠቁባቸው ኢትዮጵያ፣ ቬትናም፣ኤርትራ ደግሞ አነስተኛ ቁጥር ያለባቸው ሀገራት ናቸው
ብዙ ዜጎቻቸው በውፍረት የተጠቁባቸው ሀገራት
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ አንድ ሰው የቁመቱ እና ክብደቱ አማካኝ 30 እና ከዛ በላይ ከሆነ የውፍረት በሽታ አለበት ይባላል፡፡
እንዲሁም አንድ ሰው የቁመቱ እና ክብደቱ አማካኝ ከ25 እስከ 29 ከሆነ ከመጠን በላይ ክብደት አለበት እንደሚባልም ተገልጿል፡፡
ውፍረት እና ከመጠን በላይ ክብደት ባልተመጣጠነ ምግብ አመጋገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባለማድረግ እና ከመጠን በላይ መመገብ ምክንያቶች ይከሰታል፡፡
የውፍረት በሽታ ከደም ግፊት እና ልብ ሕመም ቀጥሎ ሶስተኛው ዓለማችን ገዳይ በሽታ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
በዓለማችን ብዙ ዜጎቻቸው በውፍረት በሽታ ከተጠቁባቸው ሀገራት መካከል ኩዌት፣ አሜሪካ፣ ሊቢያ፣ኳታር እና ባህሬን ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ድረስ ያለውን ደረጃ ሲይዙ ኢትዮጵያ፣ ቬትናም፣ኤርትራ፣ ካምቦዲያ እና ሩዋንዳ ደግሞ ዝቅተኛ የውፍረት በሽታ ተጠቂ ዜጎች ያለባቸው ሀገራት ናቸው፡፡