በመጭው ሰኞ እንደሚከሰት የሚጠበቀው የጸሀይ ግርዶች በየትኞቹ ሀገራት ይከሰታል?
በሚቀጥለው ሰኞ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የጸሀይ ግርዶሽ በርካታ የአለም ሀገራት እንደሚከስት ይጠበቃል
ሙሉ የጸሀይ ግርዶሹ የሚከሰተው በአሜሪካ ውስጥ በጠባብ ኮሪደር ሲሆን የተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራትም ከፊል ግርዶች ይታይባቸዋል ተብሏል
በነገው እለት ከፊል ወይም ሙሉ የጸሀይ ግርዶሽ ወይም ሶላር ኢክሊፕስ በበርካታ የአለም ሀገራት እንደሚከስት ይጠበቃል።
ሙሉ የጸሀይ ግርዶሹ የሚከሰተው በአሜሪካ ውስጥ በጠባብ ኮሪደር ሲሆን የተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራትም ከፊል ግርዶች እንደሚታይባቸው ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
ጸሀይ በጨረቃ ሙሉ በሙሉ ስትጋረድ የተወሰነው የሰሜን አሜሪካ ክፍል ሙሉ በሙሉ በጨለማ ይዋጣል። ጨረቃ በጸሀይ ስትሸፈን የሚያሳየውን ድንቅ ክስተት በሜክሲኮ ፖስፊክ ጠረፍ ያሉ በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይመለከቱታል ተብሏል።
በአውሮፓ የሚኖሩ ግን በዚህ ወቅት ሙሉ ግርዶች አያዩም። ነገርግን በዩናይትድ ኪንግደም(ዩኬ) ወይም አየርላንድ የሚኖሩ ሰዎች የአየሩ ጥርት ያለ ከሆነ ከፊል የጸሀይ ግርዶሽ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።
ሙሉ ግርዶሹን ለማየት እድለኛ የሚሆኑ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ሰዎች የአይናቸውን ጉዳት ለመከላከልም መነጽር መጠቀም ግድ ይላቸዋል።
ሰዎች መከላከያ መነጽር ማድረግ የሚመከሩት ግርዶሹ በሚቆይባቸው ጥቂት ደቂቃዎች ወቅት ነው።
የአሜሪካው የጠፈር ምርመር ኤጀንሲ ናሳ ግርዶሹ ከሚሰትባቸው ቦታዎች በቀጥታ ለበርካታ ሰአታት በኦንላይ በቀጥታ ያስተላልፈዋል።
ኤጀንሲው ክስተቱን በቴሌስኮፕ ቀርፆ የሚያሳይ ሲሆን ሳይንቲስቶችን እና ጠፈርተኞችን አቅርቦ ማብራሪያ እንዲሰጡ ያደርጋል።
በተጨመሪም ኤጀንሲው በግርዶሹ ወቅት ትንሽ ሮኬት ከቨርጂኒያ ዋሎፕስ ደሴት አይኖስፌር ወደተባለው የከባቢ አየር ጫፍ ያስወነጭፋል።
በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ቀለበታዊ የሚባል የጸሀይ ግርዶሽ ተከስቶ በርካታ ቦታዎች በጨለማ የዋጡበት ክስተት ይታወሳል።
በኢትዮጵያ ዋናው የጸሀይ ግርዶሽ ከ140 ከመታት በኋላ እንደሚከሰት ባለሙያዎች ተናግረዋል።