ቶዮታ እንዳይነዱ ያላቸው 50 ሺህ ተሸከርካሪዎቹ አይነተ የትኞቹ ናቸው?
ቶዮታ ከኤር ባግ ችግር ጋር በተያያዘ 50 ሺህ በአሜሪካ የሚገኙ ተሸከርካሪዎቹ እንዳይነዱ ብሏል
ኮሮላ፣ ኮሮላ ማትሪክስ እና RAV4 ቆየት ያሉ ሞዴሎች ቶዮታ ሳይስተካሉ እንዳይነዱ ከልክሏል
ቶዮታ በአሜሪካ የሚገኙ 50 ሺህ መኪናዎቹን የሚያሽከረክሩ ሰዎች ጥገና ሳይደረግላቸው እንዳይነዱ ማስጠንቀቁ ይታወሳል።
ቶዮታ የተሽከርካሪዎቹ ባለንብረቶች መኪኖቻቸውን በፍጥነት ማሽከርከር እንዲያቆሙ እና የአደጋ ጊዜ መከላከያ የአየር ከረጢት (የኤር ባግ) በአፋጣኝ እንዲያስተካክሉ አሳስቧል።
የተሸከርካሪዎች ኤር ባግ እስከሚስተካከል ድረስም ማሽከርከር እንደሌለባቸውም ነው ኩባንያው ያሳሰበው።
ቶዮታ ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው መስጠንቀቂያው የተካተቱ የመኪና ሞዴሎችም፤
2003-2004 - ኮሮላ
2003-2004 ኮሮላ ማትሪክ
2004-2005 RAV4 ናቸው።
ተሸከርካሪዎቹ የኤር ባጋቸው እድሜ እየገፋ ከመሄዱ ጋር በተያያዘ በሚፈነዳበት ጊዜ ስለታማ ስብርባሪ ቁሶችን ሊያፈናጥር ይችላል የተባለ ሲሆን፤ ስለታማ ነገሮቹ ከከባድ ጉዳት እስከ ሞት ሊያስከትሉ ይችላሉ ተብሏል።
ቶዮታ ባወጣው መግለጫው የተሸከርካሪዎቹ ባለንብረቶች የኤር ባግ ችግሩን በነጻ እስኪያስተካክሉ ድረስ እንዳይነዱ አሳስቧል።
የመኪናዎቹ ባለቤቶች ችግሩን ለማስተካከል በአካባቢያቸው ያለውን የቶዮታ መኪና የሽያጭ ወኪል ማነጋገር እንደሚችሉም ነው ኩባንያው ያስታወቀው።
በታካታ ኩባያ በተመረተው የአደጋ የአደጋ ጊዜ መከላከያ የአየር ከረጢት (የኤር ባግ) ችግር ምክንያት ከ2009 ወዲህ ከ30 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
ቶዮታ ከንድ ወር በፊትም በተሳፋሪ በኩል ያለው የአየር ከረጢት (ኤር ባግ) ላይ ካለ ችግር ጋር በተያያዘ ከ1 ሚሊየን በላይ መኪናዎችን ወደ ፋብሪካው መጥራቱ ይታወሳል።