የስልክ ቁጥር ዝርዝሮችን ወደ አዲስ ስልክ እንዴት ማስተላለፍ ይቻላል?
አዲስ ስልክ ስንገዛ የስልክ ቁጥሮችን ከድሮው ስልካችን ላይ እንዴት እናስተላልፍ የሚለው የብዙዎቻችን ጥያቄ ነው
ስልክ ቁጥሮችን በኢሜል አድራሻ መመዝገብ የስልክ ቁጥሮች ከስልክ ጋር መጥፋታቸውን ያስቀራል
አዲስ ስልክ መግዛት አስደሳች ነገር ቢሆንም ከድሮው ስልካችን ወደ አዲሱ ፋይሎችን የማስተላለፉ ጉዳይ ለብዙዎች ፈታኝና ጊዜ የሚወስድ ሊሆን ይችላል።
ምስሎች እና ሌሎች መረጃዎችን በቀላሉ የምናስተላልፍባቸው መተግበሪያዎች አሉ።
የብዙሃኑ ጥያቄ ግን ሙሉ የስልክ ቁጥር ዝርዝሮችን ወደ አዲሱ ስልካችን የምናስተላልፍበት ቀላል መንገድ አለ ወይ የሚለው ነው።
እናም አዲስ አንድሮይድ ስልክ ገዝተው ከድሮው ስልክዎ የስልክ ቁጥሮችን ማስተላለፍ ከተቸገሩ ቀጣዩን አጭር መንገድ ይከተሉ፦
በክላውድ የስልክ ቁጥር ዝርዝርን ማስተላለፍ
በቀደመው ስልካችን ላይ “ኮንታክስት ሲንክ” የሚለውን አማራጭ በመጫን በአዲሱ ስልካችን ላይ ዝርዝሩን ለማግኘት፦
1. ሴቲንግ መክፈት
2. ፓስወርድ ኤንድ አካውንትስ የሚለውን ይጫኑ፤ የዋና አካውንታችን ኢሜል አድራሻ መጫን
3. አካውንት ሲንክ ይጫኑ
4. ኮንታክስት የሚለው ላይ በመጫን የስልክ ቁጥር ዝርዝር እስኪያመጣልን መጠበቅ
5. በመጨረሻም በአዲሱ ስልካችን ላይ “ኮንታክስት ሲንክ” የሚለውን በመጫን የተወሰነ ጊዜ መጠበቅ
የስልክ ቁጥር ዝርዝርን በማውረድ ማስተላለፍ
የኢሜል አድራሻችን ከጠፋብን አልያም በድሮው ስልካችን ላይ ያሉ የስልክ ቁጥሮችን ሲንክሮናይዝ ማድረግ ካልቻልን በጎግል ኮንታክትስ አፕ የስልክ ቁጥር ዝርዝር አውርደን ወደ አዲሱ ስልካችን ማስተላለፍ እንችላለን።
1. በድሮው ስልካችን ላይ “ጎግል ኮንታክስት” የሚል መተግበሪያ ከጎግል ፕሌይ ማውረድ
2. መተግበሪያውን ከፍተን “ፊክስ ኤንድ ማኔጅ” የሚለውን መጫን
3. “ኤክስፖርት ፋይል” የሚለውን መጫን፤ የጎግል አካውንታችን በመምረጥ “ኤክስፖርት ቪሲኤፍ ፋይል”ን መንካት
4. “ሴቭ” የሚለውን በመጫን ለተወሰነ ጊዜ መጠበቅ
5. በመጨረሻም ያወረድነውን የስልክ ቁጥር ዝርዝር ወደ አዲሱ ስልካችን መላክ
የስልክ ቁጥሮችን በኢሜል አድራሻችን እንዲመዘገቡ ማድረግ ስልካችን ቢጠፋ እንኳን ወሳኝ የምንላቸው ቁጥሮችን ከማጣት የሚታደግ መሆኑንም ለማስታወስ እንወዳለን።