በዩኬ አነፍናፊ ውሾች ኮሮና ቫይረስን መለየት ይችሉ እንደሆነ ለማወቅ ምርምር እየተካሄደ ነው
በዩኬ አነፍናፊ ውሾች ኮሮና ቫይረስን መለየት ይችሉ እንደሆነ ለማወቅ ምርምር እየተካሄደ ነው
በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በልዩ ሁኔታ የሰለጠኑ የአየርመንገድ አነፍናፊ ውሾች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ መንገደኞችን መለየት መቻል ወይንም አለመቻላቸውን ለማየት ሙከራ እየተደረገ መሆኑን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ሙከራው አነፍናፊ ውሾቹ መንገደኞች ምልክት ከማሳየታቸው በፊትም ቢሆን መለየት ይችሉ እንደሆነ ያያል፡፡ አነፍናፊ ውሾችን በአየርመንግድ ማየት የተለመደ ነው፤ እፆችን፣ መሳሪያዎችንና ሌሎች በህገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ነገሮችን መለየት የተለመደ ተግባራቸው ነው፡፡
ነገርግን በልዩ ሁኔታ የሰለጠኑ ውሾች ካንሰርን፣ ወባንና ፓሪኪሰንን ጨምሮ በሽታዎችን አንዲለዩ ይሰለጥናሉ ተብሏል፡፡
የሎንዶን የጤና ኮሌጅና ትሮፒካል ሜዲሲን ተመራማሪዎች ከቻሪቲ ሜዲካል ዶግስና ከዩኬ ዱርሀም ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች የሰውነት ጠረን ስለሚቀይሩ፤ ውሾቹ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ሊጠቁሙ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
የዩኬ መንግስት ለጥናት ቡድኑ ከግማሽ ሚሊዮን ዶላር በላይ መድቧል፡፡
ይህ የመነሻ ሙከራ ስድስት ውሾችን የመለመለ ሲሆን ሲያሜያቸውም “ስድስቱ ኃያላን” ተብሏል፡፡
የጥናት ቡድኑ መሪ ተመራማሪና የሎንደኑ የጤና ኮሌጂና ትሮፒካል ሜዲሲን ክፍል ኃላፊ የሆኑት ጄምስ ሎጋን(ፕ/ር) ምርምሩ ውጤት እንደሚያመጣ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡