የግብጽ፣ ሶማሊያና ኤርትራ መሪዎች በምን ጉዳይ ላይ ተወያዩ፤ የደረሷቸው ስምምነቶስ ምንድን ናቸው?
የግብጽ፣ ሶማሊያና ኤርትራ መሪዎች በአስመራ የሶስትዮሽ ምክክር አድርገዋል
ምክክሩ የሶስቱን ሀገራት ትብብርና በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል
የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የግብጽ ፕሬዝዳንት አልቡልፈታህ አልሲሲሰ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ በአስመራ የሶስትዮሽ ምክክር አድርገዋል።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ እና የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ አስመራ ገብተው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መክረዋል።
በኤርትራና ግብጽ የሁለትዮሽ ምክክር የተነሱ ጉዳዮች
-በቀጠናው መረጋጋትን እና ትብብርን ለማጎልበት የአለም አቀፍ ህግ መሰረታዊ መርሆችን ማክበር ያለውን ጠቀሜታ አንስተው መክረዋል።
-ለክልላዊ መረጋጋት የሚያደርጉትን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል።
-የግብጽ እና የኤርትራ ህዝቦች የልማትና የብልፅግና ፍላጎት ለማሳካት በተለያዩ መስኮች የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተዋል።
-በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የፖለቲካ ምክክር ኮሚቴ ለማቋቋም የተስማሙ ሲሆን፤ በአህጉራዊ፣ ዓለም አቀፋዊ እና ጂኦፖለቲካዊ የጋራ ተጠቃሚነት ጉዳዮች ላይ ምክክር ለማድረግ የሚያግዝ ነው።
የግብጽ፣ ሶማሊያና ኤርትራ መሪዎች የሶስትዮሽ ምክክር
-የሶስቱ የሀገራ መሪዎች ለቀጣናው ሀገራት ሉዓላዊነት፣ ነፃነት እና የግዛት አንድነት መከበር የአለም አቀፍ ህግ መሰረታዊ መርሆችን የማክበር አስፈላጊነትን ምክክር አድርገዋል።
-የሶማሊያ የሚያጋጥማትን የተለያዩ የውስጥ እና የውጭ ችግሮችን ለመጋፈጥ በሶስቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል።
-የሶማሊያ ጦር ሽብርተኞችን ለማዋጋት በሚያደርገው ጥረት አስፈላጊ የሆነውን ድጋፍ ሁሉ ለማቅረብም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።
-በሱዳን ጦርነት እንዲሁም በሶማሊያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በጥልቀት መወያየታቸውን እና የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውንም አስታውቀዋል።
-በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር ሰላምና መረጋጋት ማስፈን በተለይም በባብ-አል ማንዳብ የባህር ዳርቻ የፀጥታ እና የትብብር ጉዳዮች በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ አትኩረው ውይይት አድርገዋል።
-የኤርትራ፣ የግብፅ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የጋራ የሶስትዮሽ ኮሚቴ ለማቋቋም በሁሉም መስኮች ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማድረግ ተስማምተዋል።