ትራምፕ ከፑቲን ጋር በቅርቡ የስልክ ንግግር እንደሚያደርጉ የትራምፕ አማካሪ ተናገሩ
አማካሪው እንዳሉት የሩሲያን ወታደሮች ከእያንዳንዷ ኢንች የዩክሬን ግዛት ለማስወጣት ማሰብ የማይቻል ነው
በትራምፕ ስር የሚዋቀረው አስተዳደር የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሚሆኑት ኮንግረስ ማን ማይክ ዋልዝ ጦርነቱ "የሰው ስጋ እና ሀብት እንደሚፈጨው" የአንደኛው የአለም ጦርነት አይነት እየሆነ ነው ብለዋል
ትራምፕ ከፑቲን ጋር በቅርቡ የስልክ ንግግር እንደሚያደርጉ የትራምፕ አማካሪ ተናገሩ።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በቀጣይ ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ የሰልክ ንግግር ያደጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፍተኛ የትራምፕ አማካሪ ተናግረዋል።
አማካሪው እንዳሉት የሩሲያን ወታደሮች ከእያንዳንዷ ኢንች የዩክሬን ግዛት ለማስወጣት ማሰብ የማይቻል ነው።
በቀጣይ ሳምንት የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ መሀላ የሚፈጽሙት ትራምፕ የዩክሬኑን ጦርነት በፍጥነት ለመቋጨት ቃል የገቡ ቢሆንም ያን እንዴት እንደሚያሳኩት ግልጽ አላደረጉም።
በትራምፕ ስር የሚዋቀረው አስተዳደር የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሚሆኑት ኮንግረስ ማን ማይክ ዋልዝ ጦርነቱ "የሰው ስጋ እና ሀብት እንደሚፈጨው" የአንደኛው የአለም ጦርነት አይነት እየሆነ ነው ብለዋል።
"ይህ ጦርነት የሚቆመው በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መሆኑን ሁሉም ያውቃል" ሲሉ በብሔራዊ ዘብ ኮሎኔል ሆነው ያገለገሉት ዋልዝ ተናግረዋል።
"ሩሲያን ክሪሚያን ጨምሮ ከእያንዳንዷ ኢንች የዩክሬይን ግዛት እናስወጣለን የሚለው እውነታውን ያገናዘብ አይመስለኝም። ፕሬዝደንት ትራምፕ ይህን እውነታ ያቃል፤ አለም ይህን ማወቁ ትልቅ እርምጃ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ወደፊት መሄድ አለብን።"
ስለትራምፕ እና ፑቲን ግንኙነት የተጠየቁት ዋልዝ "የስልክ ንግግር በቀጣዮቹ ቀናት ወይም ሳምንታት ይኖራል ብየ እጠብቃለሁ። ስለዚህ ይህን እንደመነሻ ወስደን ወደፊት እንገፋበታለን" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ሩሲያ በየካቲት 2022 በዩክሬን ላይ የከፈተችው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ በአስር ሽዎች እንዲገደሉ እንዲሁም የሩሲያ እና የምዕራባውያን ግንኙነት ከ1962ቱ የኩባ ሚሳይል ቀውስ ወዲህ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል።