ዶናልድ ትራምፕ የሱፐር ቦውል ጨዋታን በመታደማቸው ከፍተኛ ትችት እያስተናገዱ ነው
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሱፐር ቦውል ጨዋታን በአካል ተገኝተው በመታደም የመጀመሪያው በስልጣን ላይ ያሉ ፕሬዝደንት መሆን ችለዋል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/10/243-163123-img-20250210-152801-347_700x400.jpg)
ትራምፕ ይህን ጉብኝት ያደረጉት ወደ ሀይትሀውስ ገብተው የዲሞክራቱ ጀ ባይደን ያሳለፏቸውን ወሳኔዎች በመሻር ጭምር በርካታ ትዕዛዞችን ከስተላለፉ ከሶስት ሳምንታት በኋላ ነው
ዶናልድ ትራምፕ የሱፐር ቦውል ጨዋታን በመታደማቸው ከፍተኛ ትችት እያስተናገዱ ነው።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሱፐር ቦውል ጨዋታን በአካል ተገኝተው በመታደም የመጀመሪያው በስልጣን ላይ ያሉ ፕሬዝደንት መሆን ችለዋል።
ፕሬዝደንቱ ከብሔራዊ እግርኳስ ማህበር(ኤንኤፍኤል) ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደተወሳሰበ ባለበት ሁኔታ ጨዋታውን መመልከታቸው ድጋፍና ትችት እንዳስነሳባቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
ትራምፕ ስፖርትና ፖለቲካን አቀላቅለዋል የሚል አወዛጋቢ ታሪክም አላቸው።
ፕሬዝደንት ትራምፕ ከሴት ልዳቸው ኢቫንካና ከወንድ ልጃቸው ኢሪክ እንዲሁም በኤየርፎርስ ዋን ወደ ኒው ኦርሊንስ አጅበዋቸው ከሄዱ በርካታ የፖርላማ አባላት ጋር ጨዋታውን ተመልክተዋል። ቀዳማዊ እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ ግን በቦታው አልነበሩም።
ትራምፕ ይህን ጉብኝት ያደረጉት ወደ ሀይትሀውስ ገብተው የዲሞክራቱ ጀ ባይደን ያሳለፏቸውን ወሳኔዎች በመሻር ጭምር በርካታ ትዕዛዞችን ከስተላለፉ ከሶስት ሳምንታት በኋላ ነው።
አሜሪካውያን በእነዚህ ፖሊሲዎች ወደ ሁለት ተከፋፍለዋል። ትራምፕ ወደ ሜዳ ሲገቡ ከተሰበሰበው ህዝብ ድጋፍና ተቃውሞን አስተናግደዋል።
የቀድሞው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የዘር መድሎ ትኩረት እንዲያገኝ የአሜሪካ ህዝብ መዝሙር እየተዘመረ ባለበት ወቅት ከተንበረከኩ በኋላ ትራምፕ የእግርኳስ ማህበሩንና አባላቱን መተቸታቸው ይታወሳል።
የትራምፕ በቦታዎ ተገኝተው ጨዋታውን መመልከታቸው ብዝኻነትን፣ ፍትሃዊነትን እና አካታችነትን ለማጥፋት ባስተላለፏቸው ትዕዛዞችና እነዚህ መርሆች ለመጠበቅ በወሰነው ኤንኤፍኤል መካከል ያለውን ግልጽ ልዩነት ያሳያል ተብሏል።
የኤንኤፍኤል ኮሚሼነር ሮገር ጉዴል የብዝኻነት ፕሮግራሞችን የመቀልበስ ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል።
ትራምፕ በቦታው ተገኝተው ጨዋታ እንዲመለከቱ ለማድረግ በርካታ ሚሊዮን ዶሮች ወጭ መደረጋቸው ተዘግቧል።
ለሰክሬት ሰርቪስ 7 ሚሊዮን ዶላርና ለፕሬዝዳንታዊ እጀባና ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ ከ4-5 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ወጭ ተደርጓል ተብሏል።