ትራምፕ በተጠረጠሩበት የማጭበርበር ድርጊት ምርመራ ላይ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች “መልስ አልሰጥም” አሉ
ትራምፕ፤ ምልሽ ያልሰጠሁት የአሜሪካ ህገ-መንግስት በሰጠኝ መብት መሰረት ነው ብለዋል
"በዙሪያየ ያሉ ሰዎች ሁሉ ኢላማ ሲደረጉ ዝም ከማለት “ምንም አማራጭ አል
የኒውዮርክ አቃቤ ህግ ዶናልድ ትራምፕ የሚያስተዳድሩትን ተቋም የግብር እና ብድር እፎይታ ለማግኘት በሚል " የሚያሳስት እና ያልተገባ የንብረት ግምገማ" በማድረግ አጭበርብረዋል ሲል መክሰሱ የሚታወቅ ነው፡፡
በዚህም መሰረት ኒውዮርክ ወደ ሚገኘው ፍርድ ቤት የቀረቡት ዶናልድ ትራምፕ በተጠረጠሩበት የማጭበርበር ድርጊት መሰረት ምርመራ ላይ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች “መልስ አልሰጥም” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ትራምፕ ጉዳዩን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ “በአሜሪካ ህገ መንግስት ለእያንዳንዱ ዜጋ በተሰጡት መብቶች መሰረት፤ ጥያቄዎች ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆንኩም”ብለዋል።
ትራምፕ መልስ ላለመስጠታቸው “ቤተሰብ፣ ድርጅት እና በዙሪያየ ያሉ ሰዎች ሁሉ የፖለቲካ ፍለጎት ባላቸው ጠበቆች፣ በዐቃብያነ-ህግ የሚደገፉ የሀሰት ዜና የሚያሰራጩ ሚድያዎች ዒላማ ሲሆኑ፣ ምንም አማራጭ አልነበረኝም” የሚል ምክንያት ማቅረባቸውም ነው ፍራንስ-24 የዘገበው፡፡
በፍሎሪዳ የሚገኘውን የአሜሪካ የፌዴራል የምርመራ ቢሮ (ኤፍ.ቢ.አይ) ከቀናት በፊት የዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤትመበርበሩ የሚታወስ ነው፡
ፍተሻው ዶናልድ ትራምፕ ምናልባትም በደጋፊዎቻቸው ከተፈጸመው የካፒቶል ሂል ጥቃት ጋር በተያያዘ ከቤተ መንግስት ያሸሹት ሚስጥራዊ ሰነድ ይኖር ይሆን በሚል የተካሄደ ነው መሆኑን ሲ.ኤን.ኤን ዘግቧል፡፡
ትራምፕ ኒውዮርክ በሚገኘው ህንጻቸው ላይ ሳሉ ነው መኖሪያቸው የተፈተሸው።
"ማር-ኤ-ላጎ የሚገኘው ቅንጡ መኖሪያ ተከቦ ነው የሚገኘው፤ በብዙ የኤፍ.ቢ.አይ ፖሊሶች ተወርሮም ይገኛል" ሲሉም ነበር ዶናልድ ትራምፕ ሶሻል ትሩዝ በተሰኘ ማህበራዊ ሚዲያቸው በወቅቱ ያስታወቁት።
ድርጊቱ በቀጣዩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ (2024) እንዳይወዳደሩ ለማድረግ በማሰብ የተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
አወዛጋቢው ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2024 በሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡