አሜሪካ በአፍጋኒስታን 87 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ንብረቶችን ጥላ እንደወጣች ተገለፀ
አሜሪካ በአፍጋኒስታን ጥላው የወጣችው ባግራም ወታደራዊ ማዘዣ ለዋሸንግተን ኪሳራ እንደሆነ ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ
በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካን እያዋረዷት እንደሆነ ትራምፕ ተናግረዋል
አሜሪካ በአፍጋኒስታን 87 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ንብረቶችን ጥላ መውጣቷ ተገለጸ።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዩ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች እያካሄዱት ባለው በዚህ ቅስቀሳ ላይ እንዳሉት አሜሪካ በአፍጋኒስታን ጥላው የወጣችው ባግራም የተሰኘው ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ እጅግ ጠቃሚ እንደነበር ለጋፊዎቻቸው ተናግረዋል ሲል ራሺያን ቱዳይ ዘግቧል።
ይህ ወታደራዊ ማዘዣ በተለይም አሜሪካ ከቻይና ጋር እያደረገች ላለው ወታደራዊ እና የንግድ የበላይነት ውድድር አስፈላጊ እንደነበር ጠቁመዋል።
አሜሪካ ከፍተኛ በጀት ያፈሰሰችበት እና የቻይናን ኑክሌር መሰረተ ልማቶችን ለማጥቃት አመቺ ከሆነው ከባግራም ወታደራዊ ማዘዣ መውጣቷ ስህተት እንደሆነም የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጠቁመዋል።
የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አመራር አሜሪካንን በዓለም መድረክ እያሳነሰ መሆኑን የጠቀሱት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ እና የአሜሪካ ወዳጆች ማሳዘኑንም ተናግረዋል።
ኣሜሪካ ከአፍጋኒስታን መውጣቷ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ትልቁ ስህተት መሆኑንም ዶናልድ ትራምፕ ገልጸዋል።
አሜሪካ በአፍጋኒስታን 85 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ንብረቶችን ለታሊባን ጥላ መውጣቷን የቀድሞው ፕሬዝዳንት አክለዋል።
አሜሪካ ከ20 ዓመት የአፍጋኒስታን ቆይታ በኋላ ለታሊባን ጥላ የወጣች ሲሆን አፍጋኒስታንን እያስተዳደረ የሚገኘው ታሊባን አንደኛ ዓመቱን ከሁለት ወራት በፊት ማክበሩ ይታወሳል።