በትራምፕና በዮርዳኖስ ንጉስ አባደላ መካከል በተደረገው ውይይት ምን ጉዳዮች ተነሱ?
የዮርዳኖስ ንጉስ አባደላ 2ኛ በአሜሪካ ጉብኝት አድርገው ከትራምፕ ጋር መክረዋል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/11/252-234844-whatsapp-image-2025-02-11-at-10.47.54-pm_700x400.jpeg)
ንጉስ አባደላህ “ትራምፕ ጋዛ ላይ በያዙት እቅድ ዙሪያ የግብጽን እቅድ እንጠብቃለን” ብለዋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዮርዳኖስን ንጉስ አብዱላህ 2ኛን በዘሬው እለት በዋይት ኃውስ ተቀብለው አነጋግረዋል።
ትራምፕ ወደ ኋይት ኃውስ ከተመለሱ በኋላ እና በጋዛ ላይ አዲስ እቅድ ካስተዋወቁ ወዲህ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር የመጀመሪያውን መሪ የዮርዳኖስን ንጉስ አብዱላህ ዳግማዊን ተቀብለዋል።
ሁለቱ መሪዎች በነበራቸው ቆይታ ትራምፕ የጋዛ ነዋሪዎች የማፈናቀል እቅዳቸውን ጠንከር ያደረጉ ሲሆን፤ ግብጽ ዮርዳስም ተፈናቃዮች እንዲቀበሉ ጫና አድርገዋል።
በውይይቱ ላይም ትራም ጋዛን “የመካከለኛው ምስራቅ ሪቪዬራ” ለማድረግ የያዙትን ራዕይ ወደፊት መግፋት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
ትራምፕ ፍልስጤማውያን "በቆንጆ እና በአስተማማኝ ሁኔታ" ከጋዛ ውጪ ሌላ ቦታ እንዲኖሩ ይደረጋል ብለዋል።
በዮርዳኖስና በግብፅ ፍልስጤማውያን የሚኖሩባቸው ቦታዎች ይኖራቸዋል ያሉት ትራምፕ፤ ከግብጽ ጋር የሆነ ነገር እንደምንሰራ 99 በመቶ እርግጠኛ ነኝ ብለዋል።
ትራምፕ አክለውም እኛ ጋዛን አንገዛም፤ የራሳችን እናደርጋለን እንጂ ያሉ ሲሆን፤ ጋዛን እንወስደለን፣ የራሳችን ይሆናል፣ እንከባከበዋለን ሲሉም ተናግረዋል።
ንጉስ አብዱላህ የትራምፕን እቅድ በግልፅ ሳይደግፉ እና ሳይቃወሙ የአረብ ሀገራት እቅድ ይዘው ወደ አሜሪካ እንደሚመጡ ተናግረዋል።
ንጉሱ ሀገራቸው 2 ሺህ የታመሙ ፍልስጤማውያን ህፃናትን ከጋዛ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን ተናግረው፤ ከጋዛ የሚፈናቀሉ ሰዎች መቀበል ላይ ግን ፍቃደኝነታቸውን አልገለጹም።
ፍልስጤማውያን በዮርዳኖስ የሚኖሩበት መሬት እንዳለ የተጠየቁት ንጉስ አብደላህ ለሀገራው የሚበጀውን እንደሚያደርጉ ተናግሯል።
ንጉሱ የአረብ ሀገራት ለትራምፕ የጋዛ እቅድ ምላሽ ለመስጠት ወደ አሜሪካ እንደሚመጡ የተናገሩ ሲሆን፤ በትራምፕ ሀሳብ ዙሪያ የግብጽ እቅድ እንጠብቃለን ሲሉም ተናግረዋል።
ንጉስ አብዱላህ አክለውም አሜሪካ በጋዛ ላይ በያዘችው እቅድ ላይ “ከብዙ አገሮች ምላሽ ይኖራል” ብለዋል።