የትራምፕ መመረጥ የአውሮፓውን የጦር መሳሪያ አምራቾች እንዲያንስራሩ እንደሚያደርጋቸው ተገለጸ
አውሮፓውያን ትራምፕ አሜሪካን የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት ከሆነው ኔቶ ሊያስወጡና አውሮፓን ተጋላጭ ሊያደርጉ ይችላሉ የሚል ስጋት ገብቷዋል
ማክሮን የጦር መሳሪያ ማምረቻ ኢንዱስሪዎችን ለመደጎም ለመከላከያ ተጨማሪ ወጭ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል
የትራምፕ መመረጥ የአውሮፓውን የጦር መሳሪያ አምራቾች እንዲያንስራሩ እንደሚያደርጋቸው ተገለጸ።
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ለወታደራዊ በጀት የሚውለው በቢሊዮን ዩሮ የሚቆጠረው የግብር ከፋዮች ገንዘብ የአሜሪካን የጦር መሳሪያ ለመግዛት ብቻ ጥቅም ላይ መዋል እንደሌለበትና በሀገር ውስጥ የመከላከያ ኢንዱሰትሪዎች ላይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት መደረግ እንዳለበት በትናንትናው ተናግረዋል።
አውሮፓውያን ትራምፕ አሜሪካን የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት ከሆነው ኔቶ ሊያስወጡና አውሮፓን ተጋላጭ ሊያደርጉ ይችላሉ የሚል ስጋት ገብቷዋል።
ማክሮን አውሮፓውያን ራሳቸውን ለመከላከል በቂ ገንዘብ አይከፍሉም የሚል ቅሬታ የሚያሰሙት ትራምፕ በአለ ሲመት ከፈጸሙ ከደቂቃዎች በፊት ባደረጉት ንግግር አህጉሪቱ ተጨማሪ መክፈል አለባት ብለዋል።
ማክሮን የጦር መሳሪያ ማምረቻ ኢንዱስሪዎችን ለመደጎም ለመከላከያ ተጨማሪ ወጭ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
" 'ለጦራችን ተጨማሪ ወጭ እናውጣ ስንል' በብዙ ሀገራት 'ተጨማሪ የአሜሪካ ጦር እንግዛ' ማለት ነው" ብለዋል ማክሮን።
አውሮፓውያን ትልቅ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ያላት ፈረንሳይ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት አማራጮች እያሉ ከአሜሪካ ሲገዙ ሁል ጊዜ ቅሬታ ታሰማለች።
በ2012ዐ ጀርመን የፍራንኮ-ጣሊያን አማራጭን ወደ ጎን በመተው የአሜሪካና የእስራኤል መሳሪያ በመጠቀም 'ዩሮፒያን ስካይ ሽልድ' ስርአት ይፋ ማድረጓ በልዩ ሁኔታ ማክሮንን አበሳጮቷል። እንዲህ አይነት ስጋት ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ አሜሪካን እንደ ደህንነት ዋስትናቸው በሚቆጥሩ ሀገራት ተቀባይነት አላገኘም። ነገርግን የትራምፕ ኃይለኛ አካሄድ የአውሮፓ አባል ሀገራት የፈረንሳይን ስጋት እንዲቀበሉ እያደረጋቸው ነው። ማክሮን አክለውም አውሮፓውያን የአውሮፓውን የመከላከያ ኢንዱሰትሪ ቀላል ማድረግ አለባቸው ብለዋል።
አውሮፓ ለባህር ኃይል 47 ኢንዱስትሪዎች ያሏት ሲሆን አሜሪካ ደግሞ ስድስት ብቻ እንዳሏት ማክሮን ገልጸዋል። ማክሮን የፈረንሳይ ኩባንያዎችን ባያካትትም የአውሮፓውያን በጋራ የመሳሪያ ማምረት ስራ እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርበዋል።
"ሁልጊዜ የአውሮፓ ቀዳሚ አይደለንም፤ ነገርግን የአውሮፓ ቀዳሚ አለምአቀፋዊ ተደራሽነት እንደሚኖረው እርግጠኛ መሆን እንችላለንን።"
ማክሮን ፈረንሳይ አሁን ላይ "ከአውሮፓ ውጤታማ ጦር" እንዳላትና ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ገቢያ 2 በመቶ የሚሆነውን ለኔቶ በጀት የማዋጣት ግቧን እንዳሳካች ተናግረዋል። ማክሮን ትራምፕ ቢሮ ከገቡ በኋላ በ24 ሰአታት ውስጥ እንደሚያስቆሙት ቃል የገቡበት የዩክሬኑ ጦርነት ቢያበቃም ሩሲያ ለአውሮፓና ለሰፊው አለም የደህንነት ስጋት ሆና ትቀጥላለች ብለዋል።