የሎስ አንጀለሱ ሰደድ እሳት አደጋ ምን ላይ ይገኛል፤ ወቅታዊ ሁኔታውስ ምን ይመስላል?
14ኛ ቀኑን ያስቆጠረውና አሁንም የቀጠለው ሰደድ እሳቱ ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት አካሏል
በእሳት አደጋው 27 ሰዎች ሲሞቱ ከ16 ሺህ በላይ ህጻዎችና መኖሪያ ቤቶች በእሳት ተበልተዋል
በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማ እና አካባቢው ከ14 ቀና በፊት የጠቀሰቀሰው የሰደድ እሳት አሁን መንደዱን ቀጥሏል።
ልክ የዛሬ 2 ሳምንት የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳቱ እስካሁን ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማካለሉ ተነግሯል።
የሀገሪቱ ብሄራዊ ሜትሪዮሎጂ ኤጀንሲ በዛሬው እለት ጠዋት በፍጥነት የሚጓዝ ከባድ ነፋስ በአካባቢው እንዳለ ማሳሰቡን ተከትሎም ከፍኛ ስጋትን ደቅኗል።
የሎስ አንጀለስ ባለስልጣንት አሁንም በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው ለመልቀቅ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
የሎስ አንጀለስ የእሳት መከላከል በላሙያዎች ሌሊቱን ሊኖር ለሚችል ከባድ የእሳት አደጋ በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውንም ባለስልጣናቱ አስውቀዋል።
እሳት አደጋው ያስከተለው ጉዳት ምን ይመስላል?
በአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ ከተማ የተቀሰቀሰው የሰደድ እሳት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን እንደቀጠለ ነው።
በዚህም መሰረት የእሳት አደጋው ከተቀሰቀሰበት እለት አንስቶ እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 27 መድረሱ ተነግሯል።
በተጨማሪም ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ያካለለው የእሳት አደጋው እስካሁን ከ16 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን እና ህንጻችንም በልቷል።
በዚህ መሰረት በኢቶን እሳት 10 ሺህ መኖሪያ ቤቶች እና ህንጻዎች፣ በፓሊሳደስ እሳት 6 ሺህ 51 ቤቶች ህንጻዎች እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች ባሉ የእሳት አደጋዎች 788 ቤቶችና ህንጻዎች በእሳት መበላታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ትናት ጠዋት ባወጡት ሪፖርት አመላክተዋል።
የፓሊሳድስ እና ኢቶን ሰደድ እሳት ዛሬም መንደዱን የቀጠለ ሲሆን፤ የፓሊሳድስ እሳትን 59 በመቶ እንዲሁም የኢቶን እሳትን ደግሞ 87 በመቶ መቆጣጠር መቻሉም ተነግሯል።
በአደጋው የደረሰው ጠቅላላ ውድመት እና የኢኮኖሚ ኪሳራ 250 ቢሊዮን እና 275 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን አኩ ዌዘር ገምቷል።
የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ሁሪካን ካትሪና ካደረሰው አደጋ በመብለጥ በአሜሪካ ታሪክ እጅግ ከባድ የተፈጥሮ አደጋ ሆኖ ተመዝግቧል።