ፕሬዝደንት ትራምፕ በሩዋንዳና ዲአርሲ መካከል ያለው ቀውስ "እጅግ አሳሳቢ ነው"አሉ
በጎረቤት ሩዋንዳ ይደገፋሉ የሚባሉት የኤም23 አማጺያን በምስራቅ ዲአርሲ የምትገኘውን ጎማ የተባለችው ትልቅ ከተማ ከቀናት በፊት መቆጣጠር ችለዋል
ዲአርሲ ከእነዚህ አማጺያን ጀርባ ሩዋንዳ እጇ አለበት የሚል ክስ አቅርባለች
ፕሬዝደንት ትራምፕ በሩዋንዳና ዲአርሲ መካከል ያለው ቀውስ "እጅግ አሳሳቢ ነው"አሉ።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሩዋንዳና በዲሞክራቲክ ረፐብሊክ ኮንጎ(ዲአርሲ) መካከል ያለውን ቀውስ "እጅግ አደገኛ ነው" ሲሉ ገልጸውታል።
ትራምፕ በዋሽንግተን ከሄሊኮፕተር ጋር ተጋጭቶ ከ60 በላይ ሰዎች የሞቱበትን የአውሮፕላን አደጋ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ አሜሪካ፣ተመድና ሌሎች ሩዋንዳ እየተሳተፈችበት ነው ያሉትን የምስራቅ ዲአርሲ ግጭት ለማስቆም አቅደው እንደሆነ ተጠይቀዋል።
ትራምፕ በምላሻቸው "እየጠየቃችሁኝ ያለው ስለሩዋንዳ ነው። እጅግ አደገኛ ችግር ነው። ነገርግን አሁን ስለዚህ ጉዳይ ማውራት ተገቢ አይደለም፤ ነገርግን ችግሩ በጣም አሳሳቢ ነው" ብለዋል።
በጎረቤት ሩዋንዳ ይደገፋሉ የሚባሉት የኤም23 አማጺያን በምስራቅ ዲአርሲ የምትገኘውን ጎማ የተባለችው ትልቅ ከተማ ከቀናት በፊት መቆጣጠር ችለዋል።
በአሁኑ ወቅት አማጺያኑ ከጎ በደቡብ በኩል በመንቀሳቀስ ተጨማሪ ቦታዎችን ለመቆጣጣር እየሞከሩ ይገኛሉ።
ዲአርሲ ከእነዚህ አማጺያን ጀርባ ሩዋንዳ እጇ አለበት የሚል ክስ አቅርባለች።
አማጺያኑ ጎማ ከተማን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የተቆጡ ኮንጓውያን በሀገሪቱ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ወደ አደባባይ በመውጣት የአሜሪካ እና የፈረንሳይን ጨምሮ በርካታ ኢምባሲዎችን አጥቅተዋል።