ትራምፕ ምርጫው “በከባድ ተጭበርብሯል፤እንደ ታዳጊ ሀገር ሆነናል” አሉ
የአሜሪካ ጠቅላላ አገልግሎቶች አስተዳደር ለጆ ባይደን ምርጫ ድል እውቀና መስጠቱ ይታወሳል
ምርጫው ተጭበርብሯል የሚሉት ትራምፕ ኃይት ኃውስን ለባይደን ለመልቀቅ እንደሚቸገሩ ገልጸዋል
ምርጫው ተጭበርብሯል የሚሉት ትራምፕ ኃይት ኃውስን ለባይደን ለመልቀቅ እንደሚቸገሩ ገልጸዋል
ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንንት ዶናልድ ትራምፕ የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተጭበርብሯል፤ “እንደ ታዳጊ ሀገራትም ሆነናል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከምርጫው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የተቀበሉት ትራምፕ ምርጫው በእጅጉ በመጭበርበሩ ሽንፈትን ማመን አስቸጋሪ እንደሆነባቸው አስታውቀዋል፡፡ በኢሌክቶራል ቮት የምርጫ ውጤት መሰረት ባይደን በማሸነፋቸው ኋይት ሀውስን ይለቃሉ ወይ ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ይህንን ማድረግ ከባድ ነው ምክንያቱም በምርጫው እጅግ በጣም ከፍተኛ መጭበርበር ነበረ ብለዋል፡፡
በድጋሚ ሽንፈታቸውን እንደሚያምኑ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው ትራምፕ ሊለቁ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ እንደሚለቁ ፍንጭ ይስጡ እንጅ ምርጫው ግን መጭበርበሩን እናውቃለን ሲሉ መልሰዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ምርጫው ተጭበርብሯል ይበሉ እንጅ ይህንን የሚያመለክት የሕግ ጉዳይ በምላሻቸው አላካተቱም ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ጆ ባደን በይፋ አሸናፊነታቸውን የሚያዉጁ ከሆነ ኢሌክቶራል ኮሌጅ ትልቅ ስህተት መስራቱን ማወቅ እንዳለበትም ነው የገለጹት፡፡ ፎክስ ኒውስም በተመሳሳይ ትራምፕ ሽንፈታቸውን ለማመን ከባድ እንደሚሆንባቸው ገልጸዋል ሲል ጽፏል፡፡ ይሁንና ኢሌክቶራል ኮሌጅ ባይደን መመረጣቸውን በይፋ ከገለጸ ኋይት ሀውስን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆናቸውንም ለሪፐብሊካኖች ቅርብ የሆነው ፎክስ ኒውስ አስነብቧል፡፡
ከቀናት በፊት የአሜሪካ ጠቅላላ አገልግሎቶች አስተዳደር ለ ጆ ባይደን የምርጫ ድል ዕውቅና መስጠቱ የሚታወስ ሲሆን የተሰናባቹን እና የተመራጩን ፕሬዚዳንቶች የሽግግር ሂደት እንዲጀመር የሚያዝ ይፋዊ ደብዳቤም ጽፎ ነበር፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ግን እስካሁን ምርጫው መጭበርበሩን እየገለጹ በመሆናቸው የባይደንን አሸናፊነት አልተቀበሉም፡፡