![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/15/252-132951-whatsapp-image-2025-02-15-at-12.29.06-pm_700x400.jpeg)
“እስራኤል በጋዛ ምን ልታደርግ እንደምትችል ልነግራችሁ አልችምል” ብለዋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዛ ጉዳይ ላይ ጠንከር ያለ አቋም እንደሚይዙ አስታውቀዋል።
ትራምፕ በኦቫል ቢሯቸው ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "ዛሬ ከሰዓት ምን ላይ ምን ሊከሰት እንደሚችል አላውቅም፣ እኔ ብሆን ግን በጣም ከባድ አቋም እወስዳለሁ፤ እስራኤል ምን እንደምታደርግ ልነግራችሁ አልችልም” ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቀናት በፊት ሃማስ ታጋቾችን ዛሬ ቅዳሜ የማይለቅ ከሆነ የተኩስ አቁም ስምምቱ እንዲፈርስ ሀሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል።
"እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ሁሉም ታጋቾች እስከ ቅዳሜ ከሰአት ካልተለቀቁ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማቆም እና በሃማስ ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ተገቢው ጊዜ ይመስለኛል” ብለዋል።
ሃማስ እስራኤል ስምምነቱን ጥሳለች በሚል በዛሬው እለት የሚያካሂደውን 6ኛ ዙር ታጋቾችን የመልቀቅ መርሃ ግብር አዘግይቶት የነበረ ሲሆን፤ በኳታር እና ግብጽ አሸማጋይነት ታጋቾችን ዛሬ ለመልቀቅ ተስማምቷል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ “ሃማስ አሁን ላይ ታጋቾችን መልቀቅ እንደሚፈልግ አስታውቋል” ብለዋል።
“ሃማስ ታቾችን አንለቅም ማለትከጀመረ ግን ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ምን ሊከሰት እንደሚችል ትመለከታላችሁ” ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቅርቡ ፍሊስጤማውያንን በማስወጣት ጋዛን መቆጣጠር እንደሚፈልጉ እና ሰርጡን የመካከለኛው ምስራቅ ሪቬራ ማድረግ እንደሚፈልጉ መናገራቸው ይታወሳል።
ትራምፕ በጋዘ ላይ የያዙት ቅድ ከአረብ ሀገራ እና ከሌሎችም የዓለም ሀገራት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።