ትራምፕ አሜሪካ ከአለም ጤና ድርጅትና ከፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት እንድትወጣ ትዕዛዝ ሰጡ
ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ትናንት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል
ትራምፕ ድርጁቱ "አግባብነት ከሌለው የድርጅቱ አባላት ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ነጻ ሆኖ መንቀሳቀስ" እንዳቃተውና አሜሪካ እንደ ቻይና ካሉ ትላልቅ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ብዙ ገንዘብ እንድታዋጣ መጠየቁን ገልጸዋል
ትራምፕ አሜሪካ ከአለም ጤና ድርጅትና ከፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት እንድትወጣ ትዕዛዝ ሰጡ።
47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው በትናንትው እለት ቃለ መሃላ የፈጸሙት ዶናልድ ትራምፕ የአለምጰጤና ድርጅት የኮቪድ ወረርሽኝንና ሌሎች የጤና ጉዳዮችን በአግባቡ አልመራም በማለት አሜሪካ ከድርጅቱ እንደምትወጣ በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
ትራምፕ በርከታ በባይደን ጊዜ የነበሩ አሰራሮች ቀሪ እንዲሆኑ ያደረጉ ሲሆን አሜሪካ ወሳኝ ከተባለው የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት እንድትወጣ ትዕዛዝ አስቀምጠዋል።
ትራምፕ ድርጁቱ "አግባብነት ከሌለው የድርጅቱ አባላት ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ነጻ ሆኖ መንቀሳቀስ" እንዳቃተውና አሜሪካ እንደ ቻይና ካሉ ትላልቅ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ብዙ ገንዘብ እንድታዋጣ መጠየቁን ገልጸዋል።
"የአለም ጤና ድርጅት ጎድቶናሉ፤ ሁሉም አሜሪካን ጎድቷል። ከዚህ በኋላ ይህ አይሰራም" ሲሉ ትራምፕ ሁለተኛ የስልጣን ዘመን በዓለ ሲመታቸው ከፈጸሙ በኋላ ትዕዛዙ ላይ ፋርማቸውን ባስቀመጡበት ወቅት ተናግረዋል።
ሮይተርስ የአለም ጤና ድርጅትን ጠይቆ መልስ አለማግኘቱን ጠቅሷል።
እርምጃው አሜሪካ በ12 ወራት ውስጥ ከድርጅቱ እንድትወጣና ለስራ የሚውል ሁሉንም የገንዘብ መዋጮ እንድታቆም የሚያደርግ ነው።
አሜሪካ 18 በመቶ በማዋጣት እስካሁን ድረስ የአለም ጤና ድርጅት ትልቅ ለጋሽ ሀገር ናት። የድርጁቱ የ2024-2025 በጀት 6.8 ቢሊዮን ዶላር ነው።
የአሜሪካ መውጣት በድርጁቱ ውስጥ ያሉ መርሃግብሮችን አደጋ ውስጥ እንደሚከት በድርጅቱ ውስጥ እና ውጭ ያሉ ባለሙያዎች እየገለጹ ነው።
ትራምፕ ፊርማቸውን ያኖሩበት ትዕዛዝ የትራምፕ አስተዳደር በአለም ጤና ድርጅት ወረርሽኝ ስምምነት ዙሪያ የሚያደርገውን ድርድር ያቆማል። በትዕዛዙ መሰረት በድርጁቱ ውስጥ የሚሰሩ አሜሪካውያን ተጠርተው ሌላ ቦታ እንደሚመደቡ እንዲሁም መንግስት የድርጅቱን አስፈላጊ ተግባራት የሚከውኑ አጋሮችን እንዲፈልግ ይደረጋል።
መንግስት የአሜሪካን 2024 ግሎባል ዜልዝ ሴኩሪቲ ስትራቴጂ እንደሚገመግመው፣ እንደሚሰርዘውና እንደሚተካው ይገልጻል ትዕዛዙ።
አብዛኛው ገንዘብ ለአምአቀፍ የፖሊዮ ማጥፋት ዘመቻና ለአለምአቀፍ የክትባት ቡድን ጋቪ ቢውለም የድርጅቱ ሁለተኛ ለጋሽ ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንጄሽን ነው። የአውሮፓ ኮሚሽን እና የአለም ባንክ ለድርጅቱ በሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል። ጀርመን 3 በመቶ የሚሆነውን የአለም ጤና ድርጅት ፈንድ በማዋጣት ቀጣዩን ደረጃ ይዛለች።
የትራምፕ ከአለም ጤና ድርጅት መውጣት የማይጠበቅ አይደለም። ትራምፕ በ2020 በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ድርጅቱ "ቻይና አለምን እንድታሳስት ረድቷል" በማለት ነበር ከድርጅቱ ለመውጣት እርምጃ መውሰድ የጀመሩት።
የአምጤና ድርጅት ግን የትራምፕን ክስ አስተባብሎ፣ ቻይና መረጃውን ለአለም እንድታጋራ ጫና ማድረጉን እንደሚቀጥል መግለጹ ይታወሳል።