ቱርክ ከሶሪያው በሽር አልአሳድ መውደቅ በኋላ ተጽዕኖዋ ለምን አየለ?
የኔቶ አባል የሆነችው ቱርክ ጎረቤቷን በዲፕሎማሲ፣በኢኮኖሚና በወታደራዊ ኃይል ተጽዕኖ ለማሳደር በሚያስችል አቋም ላይ ትገኛለች
በቀድሞው የአልቃኢዳ አጋር ሀያት ታህሪር አልሻም የሚመራው አዲሱ የሶሪያ አስተዳደር ለሶሪያ በጎ እይታ አለው
የሶሪያ አማጺያን የበሽር አላሳድ አገዛዝን ከገረሰሱ በኋላ ቱርክ ሶሪያ ውስጥ ያላት ተሰሚነት ጨምሯል።
የኔቶ አባል የሆነችው ቱርክ ጎረቤቷን በዲፕሎማሲ፣በኢኮኖሚና በወታደራዊ ኃይል ተጽዕኖ ለማሳደር በሚያስችል አቋም ላይ ትገኛለች።
ቱርክ ከሶሪያ ጋር ያላት ግንኙነት እና እንዴት ተጽዕኖ ለማሳደር ተስፋ እንዳደረገች ሮይተርስ እንደሚከተለው ዳሷል
ቱርክ እንዴት አስፈላጊ ሆነች?
ከሶሪያ ጋር 911 ኪሎሜትር ድንበር የምትጋራው ቱርክ 13 ወራትን ባስቆጠረው የሶሪያ የእርስበእርስ ግጭት በሶሪያ ብሔራዊ ጦር ስር ለሚዋጉ አማጺያን ዋነኛ ደጋፊ ነበረች። ቱርክ ከሶሪያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ያቋረጠችው በ2012 ነበር። በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ዋና መጠለያና ዋና የምግብ የእርዳታ መግቢያም ነበረች ቱርክ።
ከ2016 ጀምሮ ቱርክ እንደ ብሔራዊ ስጋት በምታያቸው በሰሜን ሶሪያ በመሸጉ በርካታ የኩርድ ታጣቂዎች ላይ ከሶሪያ አጋሮቿ ጋር በመሆን ድንበር በማቋረጥ በርካታ ጥቃቶችን ከፍታለች።
በቀድሞው የአልቃኢዳ አጋር ሀያት ታህሪር አልሻም የሚመራው አዲሱ የሶሪያ አስተዳደር ለሶሪያ በጎ እይታ አለው።
ቱርክ የምትፈልገው ምንድን ነው?
ከአዲሱ አስተዳደር ጋር ጥብቅ ግንኙነት በመፍጠር ቱርክ በመልሶ ግንባታ፣ በኃይል እና በመከላከያ እና በሌሎች ዘርፎች በመሳተፍ የመጠቀም ፍላጎት አላት። የአሳድ ውድቀት ቱርክ በድንበሯ የሚንቀሳቀሰውን የኩርዲሽ ፒፕልስ ፕሮቴክሽን ዩኒት(ዋይፒጂ) ለማጥፋት እድል ይፈጥርላታል ተብሏል።
ቱርክ ዋይፒጂን ከ1984 ጀምሮ ጥቃት የከፈተባት እና በቱርክ፣ በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት በሽብር የተፈረጀው የኩርዲሽ ወርከርስ ፓርቲ(ፒኬኬ) ተጠቀጥያ አድርጋ ነው የምታየው።
ነገርግን የሶሪያን ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጥምረት የሚመራው ዋይፒጂ አሜሪካ ከእስላሚክ ስቴት ጋር በምታደርገው ውጊያ ዋነኛ አጋር ነው። ዋሽንግተን ለኩርድሽ አካል ለሆነ ቡድን የምታደርገው ድጋፍ በአሜሪካ እና አንካራ መካከል የቅራኔ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል፤ ነገርግን የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊዳን በዛሬው እለት ወደ ኃይትሀውስ የሚገቡት ትራምፕ የተለየ አካሄድ እንደሚከተሉ እናምናለን ብለዋል።
ትራምፕ እቅዳቸው ምን እንደሆነ በአደባባይ ባይናገሩም "የሶሪያን ቁልፍ የምትይዘው ቱርክ ነች"ሲሉ ተናግረዋል። በይፋ ያልተመረጠው የሶሪያ መሪ አህመድ አልሻራ ሶሪያ ፒኬኬ ቱርክን ለማጥቃት ሶሪያን እንደመነሻ እንዲጠቀም እንደማይፈለግ እየተናገረ ይገኛል። በአልሻራ የሚመሩት አማጺያን ባለፈው ወር ደማስቆን ከተቆጣጠሩ በኋላ በቱርክ የሚደገፉት ኃይሎችና በኩርድ የሚደገፉት ኃይሎች ውጊያ ገጥመዋል።
የቱርክ ደህንነት ኃላፊ ኢብራሂም ካሊን አሳድ ከወደቀ ከቀናት በኋላ በማስቆ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከፍተኛ ዲፕሎማቷ ፊዳን ደግሞ ሶሪያን የጎበኙ የመጀመሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዋል። ቱርክ ኢምባሲዋን መልሶ በመክፈት የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።