ትራምፕ ቪዲዮ እንዲሰረዝ አዘዋል የሚል ተጨማሪ ክስ ቀረበባቸው
የፕሬዝደንቱ ስታፍ ሰራተኛ የነበሩ ሰራተኛም ሰነድ በመደበቅ ተባብረዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል
ትራምፕ ባለፈው ወር በሚያሚ በቀረቡበት ወቅት ከስልጣን ከለቀቁ በኋላ በህገወጥ መንገድ ሚስጢራዊ ሰነዶችን ይዘዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ፍሎሪዳ በሚገኘው ቤታቸው አንድ ሰራተኛ ቪዲዮ እንዲሰረዝ አዘዋል የሚል ተጨማሪ ክስ ቀርቦባቸዋል።
የፕሬዝደንቱ ስታፍ ሰራተኛ የነበሩ ሰራተኛም ሰነድ በመደበቅ ተባብረዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።
በኘሬዝደንቱ ላይ የቀረቡ ክሶችን እያሳፋ ያለው የአማሪካ አቃቤ ህግ ቪዲዮው እንዲጠፋ የተደረገው ትራምፕ በምርመራ ላይ በነበሩበት ወቅት ነው ብሏል።
የአሜሪካ ልዩ አማካሪያ ጃክ ስሚዝ በትራምፕ ላይ ተጨማሪ ሶስት ክሶችን በማቅረብ አጠቃላይ በፕሬዝደንቱ ላይ የቀረቡት ክሶች 40 አድርሷቸዋል።
ፍትህ እንዲጓል በማድረግ እና ትራምፕ ሰነድ እንዲደብቁ በመርዳት በትራምፕ ማራ ላጎ ሪዞርት የጥገና ሰራተኛ የነበሩተት ካርሎስ ዲኦሊቬራም በአቃቤ ህግ ተከሰዋል።
ሮይተርስ የዲኦሊቬራ ጠበቃ መልስ እንዳልሰጠው ዘግቧል።
ዲኦልቬራ የተከሰሰው ለፈኤፍ ቢ አይ የምርመራ ሰራተኞች ሚስጢራዊ መረጃ የያዙ ሳጥኖችን በማራ ላጎ አላዘዋወርኩም በሚል ዋሽቷል በሚል ነው ።
በክሱ ላይ ዲኦሊቬራ "በፍጹም አላየሁም" የሚል መልስ ሰጥቷል።
ክሱ ይፋ የሆነው ትራምኘ ጠበቃቸው የ2020 ምርጫ ውጤትን ለመቀልበስ ሞክረዋል በሚል ምርመራ ኸሚያደርገው የፍትህ ዲፖርትመንት ጋር ተገናኝተዋል ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
ይህ በትራምፕ ላይ ሌላ የወንጀል ክስ ሊጨምር ይችላል የሚል ግምት አስከትሏል።
የትራምፕ ዘመቻ አሰባባሪ ባወጣው መግለጫ ክሱን ፕሬዝደንት ትራምፕን ለማሸማቀቅ በባይደን እና በፍትህ ክፍላቸው የቀጠለ እና የወደቀ ሙከራ ነው ሲል አጣጥሎታል።
ትራምፕ ባለፈው ወር በሚያሚ በቀረቡበት ወቅት ከስልጣን ከለቀቁ በኋላ በህገወጥ መንገድ ሚስጢራዊ ሰነዶችን ይዘዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር።ነገርግን ትራምፕ ጥፋተኛ አይደሁም ሲሉ መከራከራቸው ይታወሳል።