ዜጎች መንግስታቸውን በከፍተኛ ደረጃ የሚያምኑባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
በመንግስት አስተዳደር ዜጎች ያላቸው እርካታ እምነትን እንደሚፈጥር መረጃዎች ይጠቁማሉ
ሙስና ጦርነት እና ኢፍትሀዊነት እምነትን ከሚሸረሽሩ ቀዳሚ ምክንያቶች መካከል ናቸው
ዜጎች በመንግስታቸው ላይ የሚኖራቸው እምነት ከሀገር ሀገር ይለያያል፡፡
በመንግስት ላይ የሚፈጠር እምነት ማለት የአንድ ሀገር ዜጎች በመንግስታዊ ተቋማት አፈጻጸም ፣ የአስተዳደር ብቃት ፣ በሰላም እና ደህንነት እንዲሁም በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በጥሩ መንገድ እየተጓዙ እንደሆነ ሲሰማቸው የሚፈጠር ነው፡፡
ሙስና ፣ ጦርነት እና ብጥብጥ ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር እና ኢፍትሀዊነት በመንግስት ላይ እምነት እንዳይኖር አልያም ሰዎች እርካታ እንዳይሰማቸው ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ናቸው፡፡
ባሮሜትር ጠንካራ የማስፈጸም አቅም ያላቸው ተቋማትን የገነቡ እንዲሁም የተሻለ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት በዜጎቻቸው በመታመን በቀዳሚነት ከሚገኙት መካከል እንደሆኑ ያስቀምጣል፡፡
በተጨማሪም በአስገራሚ ሁኔታ አሀዳዊ የሚባል መንግስት ያላቸው ሀገራት በደረጃው ከፊት እንደሚገኙም መረጃው ያመላክታል፡፡
ከመንግስት ተቋማት ባለፈም በመገናኛ ብዙሀን ፣ በንግድ ተቋማት እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ ዜጎች የሚኖራቸው እምነት ከመለኪያው መስፈርቶች መካከል ተካተዋል፡፡
ሳኡዲ አረብያ ፣ ቻይና እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በ86 ፣ 85 እና 84 በመቶ በዜጎቻቸው በከፍተኛ ደረጃ የሚታመኑ መንግስታት ያሉባቸው ሀገራት ናቸው፡፡
ከአለም ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቷ አሜሪካ ከአንድ እስከ 10 ባለው ደረጃ ውስጥ ያልተካተተች ሲሆን አፍሪካም ዝቅተኛ የእምነት ደረጃ ካለባቸው የአለም ክፍሎች መካከል አንዷ እንደሆነች ተገልጿል፡፡