ትሩዝ ሶሻል ዋጋው የጨመረው የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆኑት ኢለን መስክ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ መሆናቸውን ተከትሎ ነው
የዶናልድ ትራምፕ ንብረት የሆነው ትሩዝ ሶሻል ዋጋ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር አሻቀበ፡፡
አሜሪካ ባካሄደደችው የ2020ው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅት በወቅቱ ዋነኛ እጩ የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ በጆ ባይደን መሸነፋቸውን ተከትሎ ውጤቱን በሀይል ለመለወጥ ሞክረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር፡፡
ትራምፕ ውጤቱን ለመቀየር ካደረጉት ካደረጉት ጥረት መካከል የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመጠቀም ነውጥን አበረታተዋል ተብለው የቀድሞው ትዊተር፣ ፌስቡክ እና ዩቲዮብ ላይ የነበራቸው አካውንት ታዶባቸው ነበር፡፡
በዚህ እልክም ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል የተሰኘ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያ መስርተዋል፡፡ ይሁንና ትሩዝ ሶሻል የተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጽ የታሰበውን ያህል ለውጥ ማጣት አልቻለም ነበር፡፡
ለዓመታት በኪሳራ ለይ የነበረው ይህ ትሩዝ ሶሻል 52 በመቶው የኩባንያው ድርሻ በዶናልድ ትራምፕ የተያዘ መሆኑን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
የዶናልድ ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' አዲስ ማህበራዊ ሚዲያ በተጠቃሚዎች ብዛት መጨናነቁ ተገለፀ
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆኑት ኢለን መስክ ከሰሞኑ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ መሆናቸውን ካሳወቁ በኋላ የትሩዝ ሶሻል አክስዮን ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
አሁን ላይ የትሩዝ ሶሻል ጠቅላላ ዋጋ 10 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ይህም ከኢለን መስኩ ኤክስ ወይም ትዊተር የበለጠ ዋጋ ተሰጥቶታል፡፡
አንድ የትሩዝ ሶሻል አክስዮን ዋጋ አሁን ላይ ከ52 ዶላር በላይ የደረሰ ሲሆን በተለይም ኢለን መስክ ትሩዝ ሶሻልን ሊገዙት ይችላሉ የሚል መረጃ መውጣቱ ለዋጋው መጨመር ትልቁ ምክንያት ተደርጓል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የፊታችን ማክሰኞ የሚካሄድ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሀሪስ የምርጫው ዋነኛ ተወዳዳሪዎች ናቸው፡፡