ቱርክ ከድሮን እና ሌሎች የጦር መሳሪያ ሽያጭ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች
ባይራከር የተሰኘው ቱርክ ሰራሽ ድሮን ምርቶች ተፈላጊነታቸው እየጨመረ ነው ተብሏል
ናይጀሪያ እና ማሊ በቱርክ የተመረቱ የጦር መሳሪያዎችን ከሰሞኑ ተረክበዋል
የቱርኩ ባይትራከር ድሮን ምርቶች ተፈላጊነታቸው እየጨመረ ነው ተባለ፡፡
በእስያ እና አውሮፓ አህጉራት የምትገኘው ቱርክ በሀገሯ የተመረቱ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ ላይ ትገኛለች፡፡
የወቅቱ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶሃን ቱርክ የጦር መሳሪያ ፍላጎቷን በሀገር ውስጥ ፋብሪካዎቿ ማምረት አለባቸው በሚል ነበር ፕሮጀክቱን የጀመሩት፡፡ይህ እቅዳቸው አሁን ላይ ከራስ አልፎ በዓመት ቢሊዮን ዶላሮችን ገቢ ማስገኘት የጀመረ ሲሆን ባይራክተር የተሰኘው የሰው አልባ አውሮፕላን ደግሞ ተፈላጊ ሆኗል፡፡
ሀገሪቱ ይህን ድሮን ከ32 በላይ ሀገራት የላከች ሲሆን 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘችበት ሲገለጽ ቱርክ በአጠቃላይ ወደ ውጪ ሀገራት ከላከቻቸው የጦር መሳሪያ ሽያጮች ውስጥ 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን ዴይሊ ሳባህ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ባይራክተር የተሰኘው ድሮን ለ20 ሰዓታት መብረር የሚችል ሲሆን 120 ኪሎ ግራም የሚመዝን እቃ መያዝም ይችላል፡፡
እስራኤልን ኮንነው አስተያየት በመስጠት ላይ የነበሩ የቱርክ ፓርላማ አባል በልብ ህመም ህይወታቸው አለፈ
ምርቱ በአውሮፓ፣ እስያ እና አፍሪካ ተፈላጊ እየሆነ ሲሆን ናይጀሪያ እና ማሊ ከሰሞኑ አዳዲስ ምርቶችን መረከባቸው ተገጿል፡፡
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ማሊ ስድስት ባይራክተር ድሮንን ትናንት የተረከበች ሲሆን ሌላኛዋ አፍሪካዊት ናይጀሪያ ቱርክ ሰራሽ የሆኑ የምድር እና አየር ላይ ጸረ ሽብር የጦር መሳሪያዎችን ተረክባለች፡፡
የቱርኮቹ አሲጋርድ እና ኑሮል ማኪን የተሰኙ የጦር መሳሪያ አምራች ኩባንያዎች ለናይጀሪያ 13 የጦር ታንኮችን እና ድሮኖችን ለናይጀሪያ ሰርተው ለማስረከብ የ35 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡